YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 36

36
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1በክ​ፉ​ዎች ላይ አት​ቅና፥
ዐመ​ፃ​ንም በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ አት​ቅና፤
2እንደ ሣር ፈጥ​ነው ይደ​ር​ቃ​ሉና፥
እንደ ለመ​ለመ ቅጠ​ልም ፈጥ​ነው ይረ​ግ​ፋ​ሉና።
3በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥
በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል።
4በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ልህ፥
የል​ብ​ህ​ንም መሻት ይሰ​ጥ​ሃል።
5መን​ገ​ድ​ህን ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጥ፥
በእ​ር​ሱም ታመን፥ እር​ሱም ያደ​ር​ግ​ል​ሃል።
6ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥
ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል።
7ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዛ አገ​ል​ግ​ለ​ውም።
በሕ​ይ​ወቱ ደስ ባለ​ውና#ዕብ. “መን​ገድ በቀ​ና​ች​ለት” ይላል። ዐመ​ፃን በሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ላይ አት​ቅና።
8መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥
እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና።
9ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች ይጠ​ፋ​ሉና፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን እነ​ርሱ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ።
10ኀጢ​አ​ተ​ኛም ገና ጥቂት አይ​ኖ​ርም፤
ትፈ​ል​ገ​ዋ​ለህ፥ ቦታ​ው​ንም አታ​ገ​ኝም።
11የዋ​ሆች ግን ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፥
በብ​ዙም ሰላም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
12ኀጢ​አ​ተኛ ጻድ​ቁን ይመ​ለ​ካ​ከ​ተ​ዋል፥
ጥር​ሱ​ንም በእ​ርሱ ላይ ያፋ​ጫል።
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይሥ​ቅ​በ​ታል፥
ቀኑ እን​ደ​ሚ​ደ​ርስ አስ​ቀ​ድሞ ዐው​ቆ​አ​ልና።
14ኃጥ​ኣን ሰይ​ፋ​ቸ​ውን መዘዙ፥
ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም ገተሩ
ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ይገ​ድሉ ዘንድ፥
ልበ ቅኖ​ች​ንም ይወጉ ዘንድ፤
15ሰይ​ፋ​ቸው ወደ ልባ​ቸው ይግባ፥
ቀስ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​በር።
16በእ​ው​ነት ያለ ጥቂት#ዕብ. “ለጻ​ድቅ ያለው ጥቂት” ይላል።
ከብዙ የኃ​ጥ​ኣን ሀብት ይበ​ል​ጣል።
17የኃ​ጥ​ኣን ኀይ​ላ​ቸው ይሰ​በ​ራ​ልና፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቃ​ንን ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል።
18የን​ጹ​ሓ​ንን መን​ገድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፥
ርስ​ታ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤
19በክፉ ዘመ​ንም አያ​ፍ​ሩም፤
በራብ ዘመ​ንም ይጠ​ግ​ባሉ።
20ኃጥ​ኣን ግን ይጠ​ፋሉ፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች በከ​በ​ሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠ​ፋሉ።
21ኀጢ​አ​ተኛ ይበ​ደ​ራል፥ አይ​ከ​ፍ​ል​ምም፤
ጻድቅ ግን ይራ​ራል፥ ይሰ​ጣ​ልም።
22እር​ሱን የሚ​ባ​ር​ኩት ምድ​ርን ይወ​ር​ሳ​ሉና፤
የሚ​ረ​ግ​ሙት ግን ይጠ​ፋሉ።
23የሰው አካ​ሄዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ናል፥
መን​ገ​ዱ​ንም እጅግ ይወ​ድ​ለ​ታል።
24ቢወ​ድ​ቅም አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጁን ይዞ ይደ​ግ​ፈ​ዋ​ልና።
25ጐለ​መ​ስሁ፥ አረ​ጅ​ሁም፤
ጻድቅ ግን ሲጠፋ አላ​የ​ሁም፤ ዘሩም እህ​ልን አይ​ቸ​ገ​ርም።
26ሁል​ጊዜ ይራ​ራል፤ ያበ​ድ​ራ​ልም፤
ዘሩም በበ​ረ​ከት ይኖ​ራል።
27ከክፉ ሽሽ፥ መል​ካ​ሙ​ንም አድ​ርግ፥
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትኖ​ራ​ለህ።
28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍር​ድን” ይላል። ይወ​ድ​ዳ​ልና፥
ጻድ​ቃ​ኑ​ንም አይ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ምና፤
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፤
ለን​ጹ​ሓ​ንም ይበ​ቀ​ል​ላ​ቸ​ዋል፤
የኃ​ጥ​ኣ​ንን ዘር ግን ያጠ​ፋል።
29ጻድ​ቃን ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፥
በእ​ር​ስ​ዋም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራሉ።
30የጻ​ድቅ አፉ ጥበ​ብን ይማ​ራል፥
አን​ደ​በ​ቱም ጽድ​ቅን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍር​ድን” ይላል። ይና​ገ​ራል።
31የአ​ም​ላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥
ሰኰ​ና​ውም አይ​ሰ​ና​ከ​ልም።
32ኀጢ​አ​ተኛ ጻድ​ቁን ይመ​ለ​ከ​ተ​ዋል፥
ሊገ​ድ​ለ​ውም ይወ​ድ​ዳል።
33እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አይ​ተ​ወ​ውም፥
በተ​ፋ​ረ​ደ​ውም ጊዜ አያ​ሸ​ን​ፈ​ውም።
34እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደጅ ጥናው፥ መን​ገ​ዱ​ንም ጠብቅ፥
ምድ​ር​ንም ትወ​ርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ግ​ሃል፤
ኃጥ​ኣ​ንም ሲጠፉ ታያ​ለህ።
35ኀጢ​አ​ተ​ኛን ከፍ ከፍ ብሎ፥
እንደ ሊባ​ኖስ ዛፍም ረዝሞ አየ​ሁት።
36ብመ​ለስ ግን አጣ​ሁት፤
ፈለ​ግ​ሁት፥ ቦታ​ው​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።
37ቅን​ነ​ትን ጠብቅ፥ ጽድ​ቅ​ንም እይ፤
ለሰ​ላም ሰው ቅሬት አለ​ውና።
38ዐመ​ፀ​ኞች ግን በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ፤
የኃ​ጥ​ኣ​ንም ቅሬ​ቶች ይጠ​ፋሉ።
39የጻ​ድ​ቃን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው፤
በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ጠባ​ቂ​ያ​ቸው እርሱ ነው።
40እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ቸ​ዋል፥ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም፥
ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል፥
ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም፥ በእ​ርሱ ታም​ነ​ዋ​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in