YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 146

146
የሐ​ጌና የዘ​ካ​ር​ያስ መዝ​ሙር።
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ መዝ​ሙር መል​ካም ነውና።
ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ምስ​ጋና ማቅ​ረብ ያማረ ነው።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይሠ​ራ​ታል፥
ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ይሰ​በ​ስ​ባል።
3ልባ​ቸው የቈ​ሰ​ለ​ውን ይፈ​ው​ሳል፥
ቍስ​ላ​ቸ​ው​ንም ያደ​ር​ቅ​ላ​ቸ​ዋል።
4ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሙሉ ይቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋል፥
ሁሉ​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥
ኀይ​ሉም ታላቅ ነው፥ ለጥ​በ​ቡም ቍጥር የለ​ውም።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሃ​ንን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፥
ኃጥ​አ​ንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።
7ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ስ​ጋና ዘምሩ፥#ግእዝ “ሰብ​ሕዎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሚን” ይላል።
ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በመ​ሰ​ንቆ ዘምሩ፤
8ሰማ​ዩን በደ​መ​ናት የሚ​ሸ​ፍን፥
ለም​ድ​ርም ዝና​ምን የሚ​ያ​ዘ​ጋጅ፥
ሣርን በተ​ራ​ሮች ላይ፥
ልም​ላ​ሜ​ው​ንም ለሰው ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​በ​ቅል፥
9ለእ​ን​ስ​ሶ​ችና ለሚ​ጠ​ሩት ለቍ​ራ​ዎች ጫጩ​ቶች፥
ምግ​ባ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጣ​ቸው እርሱ ነው።
10የፈ​ረ​ስን ኀይል አይ​ወ​ድ​ድም፥
በሰ​ውም ጕል​በት ደስ አይ​ለ​ውም።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ፈ​ሩት፥
በም​ሕ​ረ​ቱም በሚ​ታ​መኑ ደስ ይለ​ዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in