YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 14

14
የሕ​ዝቡ ዐመፅ
1ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ። 2የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጦ​ር​ነት እን​ሞት ዘንድ ወደ​ዚች ምድር ለምን ያገ​ባ​ናል? ሴቶ​ቻ​ች​ንና ልጆ​ቻ​ችን ለን​ጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ፤ አሁ​ንም ወደ ግብፅ መመ​ለስ አይ​ሻ​ለ​ን​ምን?” አሉ​አ​ቸው።
4እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እን​መ​ለስ” ተባ​ባሉ። 5ሙሴና አሮ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጉባኤ ፊት በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ። 6ምድ​ሪ​ቱን ከሰ​ለ​ሉት ጋር የነ​በ​ሩት የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤ 7ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ “የሰ​ለ​ል​ናት ምድር እጅግ በጣም መል​ካም ናት። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ከመ​ረ​ጠን ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ወደ​ዚች ምድር ያገ​ባ​ናል፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይሰ​ጠ​ናል። 9ነገር ግን እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አታ​ምፁ፤ እኛ እና​ጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ንና#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ እንደ እን​ጀራ ይሆ​ኑ​ል​ናል” ይላል። የም​ድ​ሪ​ቱን ሰዎች አት​ፍሩ፤ ጊዜ​አ​ቸው አል​ፎ​ባ​ቸ​ዋል፤#ዕብ. “ኀይ​ላ​ቸው ደክ​ሞ​አል” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኛ ጋር ነው፤ አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው። 10ማኅ​በሩ ሁሉ ግን “በድ​ን​ጋይ እን​ው​ገ​ራ​ቸው” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ተገ​ለጠ።
ሙሴ ስለ ሕዝቡ እንደ ጸለየ
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስ​ቈ​ጡ​ኛል? በፊ​ታ​ቸ​ውስ ባደ​ረ​ግ​ሁት ተአ​ም​ራት ሁሉ እስከ መቼ አያ​ም​ኑ​ብ​ኝም? 12በሞት እቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ አን​ተ​ንና የአ​ባ​ት​ህን ቤት ግን ለታ​ላ​ቅና ከዚህ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።
13ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን ይሰ​ማሉ፤ እኒ​ህን ሕዝብ ከእ​ነ​ርሱ በኀ​ይ​ልህ አው​ጥ​ተ​ኻ​ቸ​ዋ​ልና፤ 14የዚ​ያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝ​ብህ መካ​ከል እንደ ሆንህ ሰም​ተ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐ​ይን እን​ደ​ሚ​ተ​ያይ ተገ​ል​ጠ​ህ​ላ​ቸ​ዋል። ደመ​ና​ህም በላ​ያ​ቸው ቆመች። በቀ​ንም በደ​መና ዐምድ ፥ በሌ​ሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ በፊ​ታ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ። 15እኒ​ህን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው ብት​ገ​ድል ስም​ህን የሰሙ አሕ​ዛብ፦ 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ‘እነ​ዚ​ህን ሕዝብ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ለ​ምና በም​ድረ በዳ ገደ​ላ​ቸው’ ብለው ይና​ገ​ራሉ። 17አሁ​ንም አቤቱ፥ ኀይ​ልህ ይገ​ለጥ፤ እን​ዲህ ብለህ እንደ ተና​ገ​ርህ፦ 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓቱ የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበ​ሳን፥ መተ​ላ​ለ​ፍ​ንና ኀጢ​አ​ትን ይቅር የሚል፥ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት እስከ ሦስ​ትና አራት ትው​ልድ ድረስ በል​ጆች ላይ የሚ​ያ​መጣ ነው። 19እነ​ዚ​ህን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እን​ዳ​ል​ሃ​ቸው፥ እንደ ምሕ​ረ​ትህ ብዛት የእ​ነ​ዚ​ህን ሕዝብ ኀጢ​አት ይቅር በል።”
20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤ 21ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝ፤ ስሜም ሕያው ነው፤ በእ​ው​ነት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ምድ​ርን ሁሉ ይሞ​ላል። 22በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥ 23በእ​ው​ነት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር አያ​ዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለይ​ተው ለማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸው፥ የሚ​ያ​ው​ቀው ለሌለ ለታ​ናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለጥ​ፋት ያነ​ሳ​ሱኝ ሁሉ አያ​ዩ​አ​ትም።#ዕብ. ከግ​እ​ዙና ከግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ይለ​ያል። 24ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከ​ተ​ለኝ እርሱ ወደ ገባ​ባት ምድር አገ​ባ​ዋ​ለሁ፤ ዘሩም ይወ​ር​ሳ​ታል። 25ዐማ​ሌ​ቅና ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውም በሸ​ለቆ ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ነገ ተመ​ል​ሳ​ችሁ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።”
የዐ​መ​ፁት ሕዝብ እንደ ተቀጡ
26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 27“የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ብ​ኝን እኒ​ህን ክፉ ማኅ​በር እስከ መቼ እታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ? ስለ እና​ንተ በእኔ ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረ​ምን ሰማሁ። 28እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆ​ሮዬ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁት እን​ዲሁ በእ​ው​ነት አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 29በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የተ​ቈ​ጠ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥ​ራ​ችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እና​ንተ ያጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ች​ሁ​ብኝ፥ 30ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም። 31ንጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ ያላ​ች​ኋ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ች​ሁን እነ​ር​ሱን አገ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም የና​ቃ​ች​ኋ​ትን ምድር ይወ​ር​ሷ​ታል። 32የእ​ና​ንተ ግን በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ። 33ልጆ​ቻ​ች​ሁም በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ በድ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በም​ድረ በዳ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ ግል​ሙ​ት​ና​ች​ሁን ይሸ​ከ​ማሉ። 34ምድ​ሪ​ቱን እንደ ሰለ​ሉ​ባ​ቸው እንደ እነ​ዚያ አርባ ቀኖች ቍጥር ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ አር​ባው ቀን አርባ ዓመት፥ አንዱ ቀንም አንድ ዓመት ይሁ​ን​ባ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ የቍ​ጣ​ዬን መቅ​ሠ​ፍት ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 35እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በእኔ ላይ በተ​ሰ​በ​ሰበ በዚህ ክፉ ማኅ​በር ሁሉ ላይ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያል​ቃሉ፤ በዚ​ያም ይሞ​ታሉ።”
36ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሊሰ​ልሉ ሙሴ ልኮ​አ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት ሰዎች ስለ እር​ስዋ በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ። 37ስለ​ዚ​ያ​ችም ምድር ክፉን ነገር ተና​ገሩ፤ ስለ​ዚ​ያ​ችም ምድር ክፉ የተ​ና​ገሩ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ሠ​ፍት ሞቱ፤ ምድ​ሪቱ ግን መል​ካም ነበ​ረች።#“ምድ​ሪቱ ግን መል​ካም ነበ​ረች” የሚ​ለው በግ​እዙ እንጂ በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 38ነገር ግን ምድ​ሪ​ቱን ሊሰ​ልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ በሕ​ይ​ወት ኖሩ።
ምድ​ሪ​ቱን ለመ​ያዝ የመ​ጀ​መ​ሪያ ሙከራ
(ዘዳ. 1፥4-46)
39ሙሴም ይህን ነገር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ነገረ። ሕዝ​ቡም እጅግ አዘኑ፤ 40በነ​ጋ​ውም ማል​ደው ተነሡ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ራስ ወጥ​ተው፥ “እነሆ፥ እኛ ከዚህ አለን፤ በድ​ለ​ና​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ስፍራ እን​ወ​ጣ​ለን” አሉ። 41ሙሴም አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? ይህ ለእ​ና​ንተ መል​ካም አይ​ደ​ለም። 42እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ አት​ውጡ። 43ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ በፊ​ታ​ችሁ ናቸ​ውና በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ሆ​ንም።” 44እነ​ርሱ ግን ተደ​ፋ​ፍ​ረው ወደ ተራ​ራው ራስ ወጡ፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦ​ትና ሙሴ ከሰ​ፈሩ አል​ተ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱም። 45በዚ​ያም ተራራ ላይ የተ​ቀ​መጡ ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ ወረዱ፤ መት​ተ​ዋ​ቸ​ውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ከተ​ማም ተመ​ለሱ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in