YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 18

18
የተ​ከ​ለ​ከለ ሩካቤ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ። 3እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ እኔም ወደ እር​ስዋ እን​ደ​ማ​ገ​ባ​ችሁ እንደ ከነ​ዓን ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውም አት​ሂዱ። 4ፍር​ዴን አድ​ርጉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ትሄዱ ዘንድ ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ። 5የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።
6“ከእ​ና​ን​ተም ማንም ሰው ኀፍ​ረተ ሥጋ​ውን ይገ​ልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይ​ቅ​ረብ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ። 7የአ​ባ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋና የእ​ና​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ እና​ትህ ናትና ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ። 8የአ​ባ​ት​ህን ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነው። 9የእ​ኅ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ልጅ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ በቤት ወይም በውጭ የተ​ወ​ለ​ደች ብት​ሆን፥ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ። 10የወ​ንድ ልጅ​ህን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ ወይም የሴት ልጅ​ህን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ንተ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነውና። 11ከአ​ባ​ትህ የተ​ወ​ለ​ደ​ች​ውን የአ​ባ​ት​ህን ሚስት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ ከአ​ባ​ትህ የተ​ወ​ለ​ደች እኅ​ትህ ናት፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ። 12የአ​ባ​ት​ህን እኅት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ዘመድ ናትና። 13የእ​ና​ት​ህን እኅት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የእ​ና​ትህ ዘመድ ናትና። 14የአ​ባ​ት​ህን ወን​ድም ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ ዘመ​ድህ ናትና። 15የም​ራ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የል​ጅህ ሚስት ናት፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ። 16የወ​ን​ድ​ም​ህን ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የወ​ን​ድ​ምህ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነውና። 17የሴ​ት​ንና የሴት ልጅ​ዋን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የወ​ንድ ልጅ​ዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅ​ዋን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ትገ​ልጥ ዘንድ አታ​ግባ፤ ዘመ​ዶች ናቸው፤ ኀጢ​አት ነውና። 18በእ​ኅቷ ላይ እን​ዳ​ት​ቀና ሚስ​ትህ በሕ​ይ​ወት ሳለች የእ​ኅ​ቷን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ።
19“እር​ስ​ዋም በግ​ዳ​ጅዋ ርኵ​ሰት ሳለች ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ትገ​ልጥ ዘንድ ሳት​ነጻ በግ​ዳ​ጅዋ ወደ አለች ሴት አት​ቅ​ረብ። 20ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ሚስት ጋር አት​ተኛ፤ ዘር​ህ​ንም አት​ዝ​ራ​ባት። 21ከዘ​ር​ህም ለሞ​ሎክ አት​ስጥ#ግእዙ እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኢታ​ስ​ተ​ፃ​ምድ ወል​ደከ ለመ​ል​አክ” ይላል። የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ስም አታ​ር​ክስ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ። 22ከሴ​ትም ጋር እን​ደ​ም​ት​ተኛ ከወ​ንድ ጋር አት​ተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና። 23ዘር​ህን በእ​ር​ስዋ ላይ እን​ዳ​ት​ዘ​ራና እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ስ​ባት ወደ እን​ስሳ አት​ሂድ፤ ሴት ከእ​ርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእ​ን​ስሳ ፊት አት​ቁም፤ የተ​ጠላ ነገር ነውና።
24“ከፊ​ታ​ችሁ የማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው አሕ​ዛብ በእ​ነ​ዚህ ሁሉ ረክ​ሰ​ዋ​ልና በእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ አት​ር​ከሱ። 25ምድ​ሪ​ቱም ረከ​ሰች፤ ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ቷን በእ​ር​ስዋ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትተ​ፋ​ለች። 26ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እና​ን​ተም የሀ​ገሩ ልጆች፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የሚ​ኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ከዚህ ርኵ​ሰት ምንም አት​ሥሩ፤ 27ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ሩት የሀ​ገሩ ልጆች ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ታ​ልና፤ 28ምድ​ሪ​ቱም ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን ሕዝብ እንደ ተፋች ባረ​ከ​ሳ​ች​ኋት ጊዜ እና​ን​ተ​ንም እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ። 29ከዚህ ርኵ​ሰት ሁሉ ማና​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋ​ልና። 30ስለ​ዚህ ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በሩ ሰዎች የሠ​ሩ​ትን ጸያፍ የሆ​ነ​ውን ወግ ሁሉ እን​ዳ​ት​ሠሩ፥ በእ​ር​ሱም እን​ዳ​ት​ረ​ክሱ ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 18