YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 31

31
1“ከዐ​ይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥
ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁም፤
2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋንታ ከላይ፥
ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ ርስት ከአ​ር​ያም ምን​ድን ነው?
3ሞት ለዐ​መ​ፀኛ፥
መለ​የ​ትም ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠሩ ነው።
4እርሱ መን​ገ​ዴን የሚ​ያይ አይ​ደ​ለ​ምን?
እር​ም​ጃ​ዬ​ንስ ሁሉ የሚ​ቈ​ጥር አይ​ደ​ለ​ምን?
5ከፌ​ዘ​ኞች ጋር ሄጄ እንደ ሆነ፥
እግ​ሬም ከመ​ን​ገዱ ገለል ብላ እንደ ሆነ፥
6በእ​ው​ነ​ተኛ ሚዛን ልመ​ዘን፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅን​ነ​ቴን ያው​ቃል።
7እር​ም​ጃዬ ከመ​ን​ገዱ ፈቀቅ ብሎ እንደ ሆነ፥
ልቤም ዐይ​ኔን ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥
ጉቦም በእጄ ተጣ​ብቆ እንደ ሆነ፥
8እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብ​ላው፤
በም​ድር ላይ ሥሬ ይነ​ቀል።
9ልቤ ወደ ሌላ ወንድ ሚስት ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥
በደ​ጅ​ዋም አድ​ብቼ እንደ ሆነ፥
10ሚስቴ ሌላ​ውን ሰው ደስ ታሰኝ።
ልጆ​ቼም ይዋ​ረዱ።
11የሌ​ላ​ውን ወንድ ሚስት ማር​ከስ፥
የማ​ይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩት የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት ነው።
12ይህ በሕ​ዋ​ሳት ሁሉ የሚ​ነ​ድድ እሳት፥
የገ​ባ​በ​ት​ንም ሁሉ ከሥር የሚ​ነ​ቅል ነውና።
13“ወንድ ባሪ​ያዬ ወይም ሴት ባሪ​ያዬ በእኔ ዘንድ በተ​ም​ዋ​ገቱ ጊዜ፥
ፍር​ዳ​ቸ​ውን አዳ​ልቼ እንደ ሆነ፥
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​መ​ረኝ ጊዜ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ?
በጐ​በ​ኘኝ ጊዜስ በፊቱ ምን እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ?
15እኔን በማ​ኅ​ፀን የፈ​ጠረ እነ​ር​ሱ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን?
በማ​ኅ​ፀ​ንስ ውስጥ የሠ​ራን አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?
16“ድሆች የሚ​ሹ​ትን እን​ዳ​ያ​ገኙ አድ​ርጌ እንደ ሆነ፥
የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ዐይን አጨ​ልሜ እንደ ሆነ፥
17እን​ጀ​ራ​ዬን ለብ​ቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥
ለድ​ሃ​አ​ደ​ጉም ደግሞ ከእ​ርሱ አላ​ካ​ፈ​ልሁ እንደ ሆነ፥
18እር​ሱን ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ እንደ አባቱ ከእ​ኔው ጋር አሳ​ድ​ጌው ነበር፤
ከእ​ና​ቱም ማኅ​ፀን ከተ​ወ​ለደ ጀምሮ አሳ​ደ​ግ​ሁት።
19ራቁ​ቱን የሆ​ነው ሰው በብ​ርድ ሲሞት አይቼ፥
አላ​ለ​በ​ስ​ሁት እንደ ሆነ፥
20ድሆች አል​መ​ረ​ቁኝ እንደ ሆነ፥
በበ​ጎ​ቼም ጠጕር ትከ​ሻ​ቸው አል​ሞቀ እንደ ሆነ፥
21ብዙ ረዳት እን​ዳ​ለኝ ተማ​ምኜ
በድ​ሃ​አ​ደጉ ላይ እጄን አን​ሥቼ እንደ ሆነ፥
22ትከ​ሻዬ ከመ​ሠ​ረቷ ትው​ደቅ፥
ክን​ዴም ከመ​ገ​ና​ኛዋ ትሰ​በር።
23የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግርማ አስ​ደ​ን​ግ​ጦ​ኛ​ልና፤
በእ​ር​ሱም ከመ​ያዝ በም​ክ​ን​ያት ማም​ለጥ አል​ቻ​ል​ሁም።
24“ወር​ቄን በመ​ሬት ውስጥ ቀብሬ እንደ ሆነ፥
ዋጋው ብዙ በሆነ ዕንቍ ታም​ኜም እንደ ሆነ፥
25ሀብቴ በበዛ ጊዜ፥ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥
ስፍር ቍጥር በሌ​ለ​ውም መዝ​ገብ ላይ እጄን ጨምሬ እንደ ሆነ፥
26የሚ​ያ​በራ ፀሐይ እን​ደ​ሚ​ጠፋ
ጨረ​ቃም እን​ደ​ም​ት​ጨ​ልም አላ​ይ​ምን?#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ልዩ​ነት አለው።
በራ​ሳ​ቸው ለመ​ኖር ኀይል የላ​ቸ​ው​ምና፥
27ልቤ በስ​ውር ተታ​ልሎ እንደ ሆነ፥
በአ​ፌም ላይ እጄን አኑሬ ስሜ እንደ ሆነ፥
28በል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዋ​ሸሁ ነበ​ርና
ይህ ደግሞ ትልቅ በደል ይሁ​ን​ብኝ።
29በጠ​ላቴ ውድ​ቀት ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥
በል​ቤም እሰይ ብዬ እንደ ሆነ፥
30ጆሮዬ መር​ገ​ሜን ትስማ፤
በወ​ገ​ኔም መካ​ከል ክፉ ስም ይው​ጣ​ልኝ።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ልዩ​ነት አለው።
31“ቤተ ሰቦቼ እኔ ስራ​ራ​ላ​ቸው፥
ሥጋ​ውን እን​በላ ዘንድ ማን በሰ​ጠን ብለው እንደ ሆነ፥
32መጻ​ተ​ኛው ግን በሜዳ አያ​ድ​ርም ነበር፥
ደጄ​ንም ለመ​ጣው ሁሉ እከ​ፍት ነበር፤
33ታላቅ በደ​ልም በድዬ እንደ ሆነ፥
ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሰውሬ እንደ ሆነ፥
34ከብዙ ሕዝብ የተ​ነሣ በፊ​ታ​ቸው ለመ​ና​ገር አፍሬ እንደ ሆነ፥
ድሃ​ውም ከደጄ ባዶ​ውን ወጥቶ እንደ ሆነ፥#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
35የሚ​ያ​ደ​ም​ጠ​ኝን ማን በሰ​ጠኝ!
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጅ አል​ፈ​ራሁ እንደ ሆነ፥
የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​ብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖ​ረኝ!
36በት​ከ​ሻዬ ላይ እሸ​ከ​መው ነበር፥
አክ​ሊ​ልም አድ​ርጌ በራሴ አስ​ረው ነበር፥
በብ​ዙ​ዎ​ችም መካ​ከል አነ​ብ​በው ነበር፤
37ከባለ ዕዳዬ የም​ቀ​በ​ለው ሳይ​ኖር
ቀድ​ጀው እመ​ለ​ሳ​ለሁ።#ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ጋር አይ​መ​ሳ​ሰ​ልም።
38“እር​ሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ እንደ ሆነ፥
ትል​ሞ​ች​ዋም በአ​ንድ ላይ አል​ቅ​ሰው እንደ ሆነ፥
39ፍሬ​ዋን ለብ​ቻዬ ያለ ዋጋ በልቼ እንደ ሆነ፥
ባለ መሬ​ቱ​ንም አባ​ርሬ ነፍ​ሱን አሳ​ዝኜ እንደ ሆነ፥
40በስ​ንዴ ፋንታ እን​ክ​ር​ዳድ፥
በገ​ብ​ስም ፋንታ ኵር​ን​ችት ይብ​ቀ​ል​ብኝ።”
ኢዮ​ብም ነገ​ሩን ፈጸመ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽ​ሐፈ ኢዮብ 31