YouVersion Logo
Search Icon

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 12

12
ጌታ​ች​ንን ሽቱ ስለ ቀባ​ችው ሴት
1ፋሲካ ከሚ​ው​ል​በት ከስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው አል​ዓ​ዛር ወደ ነበ​ረ​በት ወደ ቢታ​ንያ መጣ። 2በዚ​ያም ምሳ አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ማር​ታም ታሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ አብ​ረ​ውት ምሳ ከበ​ሉ​ትም አንዱ አል​ዓ​ዛር ነበር። 3#ሉቃ. 7፥37-38። ማር​ያም ግን ዋጋዉ የከ​በ​ረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናር​ዶስ ሽቱ ወሰ​ደ​ችና የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እግር ቀባ​ችው፤ በፀ​ጕ​ሯም አሸ​ችው፤ የዚያ ሽቱ መዓ​ዛም ቤቱን መላው። 4ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ የነ​በረ ያሲ​ዘው ዘንድ ያለው የስ​ም​ዖን ልጅ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ግን እን​ዲህ አለ። 5“ለነ​ዳ​ያን ይሰጥ ዘንድ ይህን ሽቱ ለሦ​ስት መቶ ዲናር ለምን አል​ሸ​ጡ​ትም?” 6ይህ​ንም ያለ፥ ድሆች አሳ​ዝ​ነ​ውት አይ​ደ​ለም፤ ሌባ ነበ​ርና፥ ሙዳየ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ሲጠ​ብቅ በው​ስጡ ከሚ​ገ​ባው ይወ​ስድ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ነው እንጂ። 7ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ለም​ቀ​በ​ር​በት ቀን ትጠ​ብ​ቀው ዘንድ ተዉ​አት። 8#ዘዳ. 15፥11። ድሆች ግን ዘወ​ትር አብ​ረ​ዋ​ችሁ አሉ፤ ዘወ​ት​ርም ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ መል​ካም ታደ​ር​ጉ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤#“ዘወ​ት​ርም ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ መል​ካም ታደ​ር​ጉ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። እኔን ግን ዘወ​ትር የም​ታ​ገ​ኙኝ አይ​ደ​ለም።”
9ከአ​ይ​ሁ​ድም ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ እን​ዳለ በዐ​ወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመ​ጡ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለማ​የት ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣ​ዉን አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ። 10የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችም አል​ዓ​ዛ​ርን ሊገ​ድ​ሉት ተማ​ከሩ። 11ከአ​ይ​ሁድ ብዙ​ዎች ስለ እርሱ እየ​ሄዱ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ያምኑ ነበ​ርና።
ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ መግ​ባቱ
12በማ​ግ​ሥ​ቱም ለበ​ዓል መጥ​ተው የነ​በሩ ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ደ​ሚ​መጣ በሰሙ ጊዜ፥ 13#መዝ. 117፥25-26። የዘ​ን​ባባ ዛፍ ዝን​ጣፊ ይዘው “ሆሣ​ዕና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የአ​ህያ ውር​ንጫ አግ​ኝቶ በእ​ር​ስዋ ላይ ተቀ​መጠ። 15#ዘካ. 9፥9። “የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ አት​ፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉ​ሥሽ በአ​ህያ ውር​ንጫ ተቀ​ምጦ ይመ​ጣል” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ 16ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነገር አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከከ​በረ በኋላ በዚያ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ፥ ይህ​ንም እንደ አደ​ረ​ጉ​ለት ትዝ አላ​ቸው። 17ከዚ​ያም አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት ሕዝብ አል​ዓ​ዛ​ርን ከመ​ቃ​ብር እንደ ጠራው፥ ከሙ​ታ​ንም እንደ አስ​ነ​ሣው መሰ​ከ​ሩ​ለት። 18ስለ​ዚ​ህም ነገር ሕዝቡ ሁሉ ሊቀ​በ​ሉት ወጡ፤ ይህን ተአ​ም​ራት እንደ አደ​ረገ ሰም​ተ​ዋ​ልና። 19ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “የም​ታ​ገ​ኙት ምንም ጥቅም እን​ደ​ሌለ ታያ​ላ​ች​ሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከ​ት​ሎ​ታል” ተባ​ባሉ።
ለበ​ዓል ስለ መጡ ሰዎች
20ከጽ​ርዕ ሰዎ​ችም ይሰ​ግዱ ዘንድ ለበ​ዓል የወጡ ነበሩ። 21እነ​ር​ሱም ከገ​ሊላ፥ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊል​ጶስ ሄደው፥ “አቤቱ፥ ጌታ ኢየ​ሱ​ስን ልና​የው እን​ወ​ድ​ዳ​ለን” ብለው ለመ​ኑት። 22ፊል​ጶ​ስም ሄዶ ለእ​ን​ድ​ር​ያስ ነገ​ረው፤ እን​ድ​ር​ያ​ስና ፊል​ጶ​ስም ሄደው ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ነገ​ሩት። 23ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “አሁን የሰው ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ጊዜው ደረሰ። 24እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የስ​ንዴ ቅን​ጣት በም​ድር ላይ ካል​ወ​ደ​ቀ​ችና ካል​ሞ​ተች ብቻ​ዋን ትኖ​ራ​ለች፤ ከሞ​ተች ግን ብዙ ፍሬን ታፈ​ራ​ለች። 25#ማቴ. 10፥39፤ 16፥25፤ ማር. 8፥35፤ ሉቃ. 9፥24፤ 17፥33። ነፍ​ሱን የሚ​ወ​ዳት ይጥ​ላ​ታል፤ በዚህ ዓለም ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ይጠ​ብ​ቃ​ታል። 26እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።
27“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ። 28አባት ሆይ፥ ልጅ​ህን#በግ​ሪኩ እና በአ​ብ​ዛ​ኛው የግ​እዝ ዘርዕ “ስም​ህን” ይላል። አክ​ብ​ረው።” ከሰ​ማ​ይም፥ “አከ​በ​ር​ሁህ፤ ደግ​ሞም እን​ደ​ገና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤” የሚል ቃል መጣ። 29በዚያ ቆመው ይሰሙ የነ​በሩ ሕዝብ ግን “ነጐ​ድ​ጓድ ነው” አሉ፤ “መል​አክ ተና​ገ​ረው” ያሉም አሉ። 30ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ቃል የመጣ ስለ እና​ንተ ነው እንጂ ስለ እኔ አይ​ደ​ለም። 31አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደረሰ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ የዚ​ህን ዓለም ገዥ ወደ ውጭ አስ​ወ​ጥ​ተው ይሰ​ዱ​ታል። 32እኔም ከም​ድር ከፍ ከፍ ካልሁ ሁሉን ወደ እኔ እስ​ባ​ለሁ።” 33ይህ​ንም ያለ በምን ዐይ​ነት ሞት ይሞት ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው ነው። 34#መዝ. 109፥4፤ ኢሳ. 9፥7፤ ሕዝ. 37፥25፤ ዳን. 7፥14። ሕዝ​ቡም፥ “እኛስ ክር​ስ​ቶስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ኖር በኦ​ሪት ሰም​ተን ነበር፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አንተ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ አለው’ ትለ​ና​ለህ? እን​ግ​ዲህ ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለ​ሱ​ለት። 35ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤ 36የብ​ር​ሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ በብ​ር​ሃን እመኑ” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ ሄደ፤ ተሰ​ወ​ራ​ቸ​ውም። 37ይህ​ንም ያህል ተአ​ም​ራት በፊ​ታ​ቸው ሲያ​ደ​ርግ አላ​መ​ኑ​በ​ትም። 38#ኢሳ. 53፥1። “አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን ማን ያም​ነ​ናል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንድ ለማን ተገ​ለጠ?” ያለው የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ቃል ይደ​ርስ ዘንድ። 39ስለ​ዚ​ህም ማመን ተሳ​ና​ቸው፤ ኢሳ​ይ​ያስ ዳግ​መኛ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና። 40#ኢሳ. 6፥10። “በዐ​ይ​ና​ቸው አይ​ተው፥ በል​ባ​ቸ​ውም አስ​ተ​ው​ለው እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ታወሩ፤ ልባ​ቸ​ውም ደነ​ደነ።” 41ኢሳ​ይ​ያስ ጌት​ነ​ቱን አይ​ቶ​አ​ልና፥ ይህን ተና​ገረ፤ ስለ እር​ሱም መሰ​ከረ። 42ከሕ​ዝቡ አለ​ቆ​ችም ያመ​ኑ​በት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከም​ኵ​ራብ አስ​ወ​ጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ሰ​ዱ​አ​ቸው በፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ምክ​ን​ያት አል​መ​ሰ​ከ​ሩ​ለ​ትም። 43ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና።
44ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “በእኔ የሚ​ያ​ምን በላ​ከ​ኝም ነው እንጂ በእኔ ብቻ የሚ​ያ​ምን አይ​ደ​ለም። 45እኔን ያየ የላ​ከ​ኝን አየ። 46በእኔ የሚ​ያ​ምን ሁሉ በጨ​ለማ እን​ዳ​ይ​ኖር ብር​ሃን እኔ ወደ ዓለም መጣሁ። 47ቃሌን ሰምቶ የማ​ይ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እኔ የም​ፈ​ር​ድ​በት አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ዓለ​ምን ላድን እንጂ በዓ​ለም ልፈ​ር​ድ​በት አል​መ​ጣ​ሁ​ምና። 48የሚ​ክ​ደ​ኝን፥ ቃሌ​ንም የማ​ይ​ቀ​በ​ለ​ውን ግን የሚ​ፈ​ር​ድ​በት አለ፤ እኔ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ቃል እርሱ በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን ይፈ​ር​ድ​በ​ታል። 49የተ​ና​ገ​ር​ሁት ከእኔ የሆነ አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የላ​ከኝ አብ እን​ድ​ና​ገር፥ እን​ዲ​ህም እን​ድል እርሱ ትእ​ዛ​ዝን ሰጠኝ። 50ትእ​ዛ​ዙም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም የም​ና​ገ​ረ​ውን አብ እን​ዳ​ለኝ እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in