ወደ ዕብራውያን 10
10
ስለ ኦሪት
1ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፤ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም። 2#ምዕ. 10 ቍ. 2 በግሪኩ ልዩ ነው።ይህስ ባይሆን ከሚሠዉት መሥዋዕት ባረፉ ነበር፥ ለሚሠዉት ኀጢአታቸውን ያስተሰርይላቸው ነበርና፥ ባአንድ ጊዜም ያነጻቸው ነበርና። 3ነገር ግን በዚያው መሥዋዕት በየዓመቱ የኀጢአት መታሰቢያ አድርገው የሚያቀርቡት ነበራቸው። 4የላምና የፍየል ደም ኀጢአትን ሊያስተሰርይ አይችልምና። 5#መዝ. 39፥6-8። ስለዚህም ወደ ዓለም በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ አለ፥ “መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም፤ ሥጋን አለበስኸኝ#ግሪኩ “ሥጋን አዘጋጀህልኝ እንጂ” ይላል። እንጂ። 6በሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ኀጢአት በሚቀርበው መሥዋዕት ደስ አላለህም። 7ያንጊዜ እነሆ፥ በመጽሐፍ ራስ ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን አደርግ ዘንድ መጥቻለሁ አልሁ።” 8በዚህ ላይ “መሥዋዕትንና መባን፥ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም፥ ስለ ኀጢአትም የሚሠዋ መሥዋዕትን አልወደድህም፤ በእርሱም ደስ አላለህም” ብሎ ተናገረ፤ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡ ናቸው። 9ከዚህ በኋላ፥ “አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን አደርግ ዘንድ እነሆ፥ መጣሁ” አለ፤ ይህ ቃል የኋለኛውን ያቆም ዘንድ የፊተኛውን ያፈርሳል። 10በፈቃዱም አንድ ጊዜ በተደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋዉ ቍርባን ተቀደስን።
11 #
ዘፀ. 29፥38። ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዘወትር እያገለገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢአት ማስተስረይ የማይቻላቸውን እነዚያን መሥዋዕቶች ብቻም ይሠዋ ነበር። 12እርሱ ግን ስለ ኀጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘለዓለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ። 13#መዝ. 109፥1። እንግዲህ ጠላቶቹ ከእግሩ በታች እስኪወድቁ ድረስ ይጠብቃል። 14#ግሪኩ “አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን ለዘለዓለም ፍጹማን አድርጓቸዋል” ይላል። ለሚቀደሱትም ለዘለዓለም የምትሆን አንዲት መሥዋዕትን ሠዋ። 15መንፈስ ቅዱስም ምስክራችን ነው። 16#ኤር. 31፥33። “ከእነዚያ ወራቶች በኋላ የምገባላቸው ኪዳን ይህቺ ናት ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልባቸው አኖረዋለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ካለ በኋላ። 17#ኤር. 31፥34። ከእንግዲህ ወዲህ ኀጢአታቸውንና በደላቸውን ደግሜ አላስብባቸውም” ብሏል። 18እንዲህም ኀጢአት የሚሰረይ ከሆነ፥ እንግዲህ ወዲህ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት አያስፈልግም።
ስለ ወንጌል ካህናት
19እንግዲህ ወንድሞቻችን ሆይ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ወደ መቅደስ ለመግባት ባለሙአልነት አለን። 20በሥጋው መጋረጃ በኩል የሕይወትንና የጽድቅን መንገድ ፈጽሞ አድሶልናልና። #ግሪኩ “በሐዲስና በሕያው መንገድ በሥጋው መጋረጃ በኩል ...” ይላል። 21በእግዚአብሔር ቤት ታላቅ ካህን አለን። 22#ዘሌ. 8፥30፤ ሕዝ. 36፥25። እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ። 23እንግዲህ የማይናወጠውን የተስፋችንን እምነት እናጽና፤ ተስፋ የሰጠ እርሱ የታመነ ነውና። 24በፍቅርና በበጎ ምግባርም ከባልንጀሮቻችን ጋር እንፎካከር። 25ሌሎች ልማድ አድርገው እንደ ያዙት ማኅበራችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
26እውነትን ካወቅናት በኋላ፥ ተጋፍተን ብንበድል ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት አይኖርም። 27#ኢሳ. 26፥11። ነገር ግን የሚያስፈራ ፍርድ ከሓዲዎችንም የሚበላቸው የቅናት እሳት ይጠብቃቸዋል። 28#ዘዳ. 17፥6፤ 19፥15። ከሙሴ ሕግ የተላለፈ ቢኖር ሁለት፥ ወይም ሦስት ምስክሮች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይሞታል። 29#ዘፀ. 24፥8። የእግዚአብሔርን ልጅ የከዳ፥ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? 30#ዘዳ. 32፥35-36። “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔም ብድራትን እመልሳለሁ፥” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ዳግመኛም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል።” 31በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው።
32እናንተ የተጠመቃችሁበትንና ብዙ መከራ የታገሣችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ፤ 33እናንተ ተሰድባችሁ ነበር፤ መከራም አጽንተውባችሁ ነበር፤ ተዘባብተውባችሁም ነበር፤ በዚህም መንገድ እንዲህ ከሆኑት ጋር ተባብራችሁ ነበር። 34በእስራቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመከራ ተባብራችኋል፤ የገንዘባችሁንም መዘረፍ በደስታ ተቀብላችኋል፤ በሰማያት ለዘለዓለም የሚኖር ከዚህ የሚበልጥና የተሻለ ገንዘብ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና። 35ትልቁን ዋጋችሁን የምታገኙባትን መታመናችሁን አትጣሉ። 36ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን ተስፋ ታገኙ ዘንድ መታገሥ ያስፈልጋችኋል። 37“ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚመጣውም ፈጥኖ ይደርሳል፥ አይዘገይምም። 38#ዕን. 2፥3-4። ጻድቅ በእምነት ይድናል፤ ወደኋላ ቢመለስ ግን ልቡናዬ በእርሱ ደስ አይላትም።”
39እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑት ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉት አይደለንም።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 10: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in