YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 9

9
ምዕ​ራፍ 9
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኖኅ የሰ​ጠው ቃል ኪዳን
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም። 2አስ​ፈ​ሪ​ነ​ታ​ች​ሁና አስ​ደ​ን​ጋ​ጭ​ነ​ታ​ችሁ በም​ድር አራ​ዊት፥ በሰ​ማይ ወፎች፥ በም​ድር ላይ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም፥ በባ​ሕር ዓሦ​ችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነ​ር​ሱ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ። 3ሕይ​ወት ያለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ መብል ይሁ​ና​ችሁ፤ ሁሉ​ንም እንደ ለመ​ለመ ቡቃያ ሰጠ​ኋ​ችሁ። 4ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤ 5ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ። 6የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና። 7እና​ን​ተም ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።”
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ለል​ጆቹ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦ 9“እኔም እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን ከእ​ና​ንተ ጋር፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ከዘ​ራ​ችሁ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ 10ከእ​ና​ንተ ጋር ላሉ​ትም፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ሁሉ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ከመ​ር​ከብ ለወ​ጡት ለወ​ፎች፥ ለእ​ን​ስ​ሳ​ትም፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ለማ​ን​ኛ​ውም ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይሆ​ናል። 11ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ውም ሁሉ ዳግ​መኛ በጥ​ፋት ውኃ አይ​ጠ​ፋም፤ ምድ​ር​ንም ለማ​ጥ​ፋት ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃ አይ​ሆ​ንም።” 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለኖኅ አለው፥ “በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትው​ልድ የማ​ደ​ር​ገው የቃል ኪዳኔ ምል​ክት ይህ ነው፤ 13ቀስ​ቴን በደ​መና አኖ​ራ​ለሁ፤ የቃል ኪዳ​ኔም ምል​ክት በእ​ኔና በም​ድር መካ​ከል ይሆ​ናል። 14በም​ድር ላይ ደመ​ናን በጋ​ረ​ድሁ ጊዜ ቀስቴ በደ​መ​ናው ትታ​ያ​ለች፤ 15በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ሕያው ነፍስ ባለ​ውም ሥጋ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ው​ንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃን አላ​መ​ጣም። 16ቀስ​ቴም በደ​መና ትሆ​ና​ለች፤ በእ​ኔና በም​ድር መካ​ከል፥ በም​ድር ላይ በሚ​ኖር ሥጋ ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ለማ​ሰብ አያ​ታ​ለሁ።” 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ “በእ​ኔና በም​ድር ላይ በሚ​ኖር፥ ሥጋ ባለው ሁሉ መካ​ከል ያጸ​ና​ሁት የቃል ኪዳን ምል​ክት ይህ ነው” አለው።
ኖኅና ልጆቹ
18ከመ​ር​ከብ የወ​ጡት የኖኅ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከ​ነ​ዓን አባት ነው። 19በም​ድር ሁሉ ላይ የተ​በ​ተኑ የኖኅ ልጆች እነ​ዚህ ሦስቱ ናቸው።
20ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይ​ንም ተከለ። 21ከወ​ይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ ዕራ​ቁ​ቱን ሆነ። 22የከ​ነ​ዓን አባት ካምም የአ​ባ​ቱን ዕራ​ቁ​ት​ነት አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁ​ለቱ ወን​ድ​ሞቹ ነገ​ራ​ቸው። 23ሴምና ያፌ​ትም ልብስ ወስ​ደው በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ አደ​ረጉ፤ የኋ​ሊ​ትም ሄደው የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ዕራ​ቁ​ት​ነት አለ​በሱ፤ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ኋላ ነበር፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም ዕራ​ቁ​ት​ነት አላ​ዩም። 24ኖኅም ከወ​ይኑ ስካር በነቃ ጊዜ፥ ታናሹ ልጁ ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ዐወቀ።
25ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።” 26እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሴም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን። 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ፌ​ትን ሀገር ያስፋ፤ በሴ​ምም ድን​ኳን ይደር፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን።”
28ኖኅም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ። 29ኖኅም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in