ኦሪት ዘፍጥረት 36
36
የዔሳው ትውልድ
(1ዜ.መ. 1፥34-37)
1ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ እንዲህ ነው። 2ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥ 3የይስማኤልን ልጅ የናቡአት እኅት ቤሴሞትን። 4ሐዳሶ ለእርሱ ኤልፋዝን ወለደች፤ ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ 5ኤሌባማም ዮሔልን፥ ይጉሜልን፥ ቆሬንም ወለደች። በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው። 6ዔሳውም ሚስቶቹን፥ ወንዶች ልጆቹንና ሴቶች ልጆቹን፥ ቤተ ሰቡንም ሁሉ፥ እንስሶቹንም ሁሉ፥ በከነዓንም ሀገር ያገኘውን ገንዘቡን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ፊት ከከነዓን ሀገር ሄደ። 7ከብታቸው ስለበዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልቻሉም፤ በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም። 8ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፤ ዔሳውም ኤዶም ነው።
9በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም እንዲህ ነው። 10የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው፤ የዔሳው ሚስት የሐዳሶ ልጅ ኤልፋዝ፤ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል። 11የዔሳው ልጅ የኤልፋዝ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ። 12ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው። 13የዔሳው ልጅ#“የዔሳው ልጅ” በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። የራጉኤል ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሲም፥ ሞዛህ፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። 14የሴቤጎን ልጅ የሐና ልጅ የዔሳው ሚስት የኤሌባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ለዔሳውም ዮሔልን፥ ዩጉሜልን፥ ቆሬን ወለደች።
15የዔሳው ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስፍን፥ ኦሜር መስፍን፥ ሳፍር መስፍን፥ ቄኔዝ መስፍን፥ 16ቆሬ መስፍን፥ ጎቶን መስፍን፥ አማሌቅ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የሓዳሶ ልጆች ናቸው ። 17የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ናሖት መስፍን፥ ዛራ መስፍን፥ ሲን መስፍን፥ ሞዛህ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። 18የዔሳው ሚስት የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስፍን፥ ይጉሜል መስፍን፥ ቆሬ መስፍን፤ የዔሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው። 19የዔሳው ልጆችና መስፍኖቻቸው እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም የኤዶም ልጆች ናቸው።
የሴይር ዘሮች
(1ዜ.መ. 1፥38-42)
20በዚያች ሀገር የተቀመጡ የሖሪያዊው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሉጣን፥ ሦባን፥ ሳባቅ፥ አናም፥ 21ዲሶን፥ ኤሶር፥ ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም ምድር የሖሪያዊው የሴይር ልጆች መሳፍንት ናቸው። 22የሉጣን ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሖሪ፥ ሃማን ናቸው፤ የሉጣንም እኅት ትምናዕ ናት። 23የሦባን ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ኤቤል፥ ሳፋር፥ አውናም። 24የሳባቅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ኢኣ፥ ዓናን፤ ይህም ዓናን በምድረ በዳ የአባቱን የሳባቅን አህዮች ሲጠብቅ ፍል ውኃዎችን#በግእዙ “ያሜን” ይላል። ያገኘ ነው። 25የዓናን ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዲሶን፤ የዓናን ሴት ልጅ ኤሌባማ። 26የዲሶንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሕምዳን፥ አስባን፥ ቤዖር፥#“ቤዖር” በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። ይትራን፥ ክራን። 27የኤሶር ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ከልሐን፥ ዛኦን፥ ዓቃን። 28የሪሶን#በግእዙ “ዲሳን” ይላል። ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዑሳ፥ አራን። 29የሖሪ መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ሉጣን መስፍን፥ ሦባን መስፍን፥ ሳባቅ መስፍን፥ ዓናን መስፍን፥ 30ዲሶን መስፍን፥ ኤሶር መስፍን፥ ሪሶን መስፍን፤ በሴይር ምድር በየሹመታቸው መሳፍንት የሆኑ የሖሪ መሳፍንት እነዚህ ናቸው።
የኤዶም ነገሥታት
(1ዜ.መ. 1፥43-54)
31በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ሀገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። 32በኤዶምም የቤዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ፤ የከተማዋም ስም ዴናባ ናት። 33ባላቅም ሞተ፤ በእርሱ ፈንታም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ። 34ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የቴማኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ። 35ሑሳምም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የገደለ የቤዳድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማዋም ስም ዓዊት ተባለ። 36ዓዳድም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የምስሬቃው ሠምላ ነገሠ። 37ሠምላም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ በወንዝ አጠገብ ካለችው ከርኆቦት ሳኦል ነገሠ። 38ሳኦልም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የዓክቦር ልጅ በአልሐናን ነገሠ። 39የአክቦር ልጅ በአልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስቱም የሜዛአብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ምኤጠብኤል ትባላለች።
40የዔሳውም የመሳፍንቱ ስም በየነገዳቸው፥ በየስፍራቸው፥ በያገራቸውና በየሕዝባቸው ይህ ነው፤ ትምናዕ መስፍን፥ ዓልዋ መስፍን፥ ኤቴት መስፍን፥ 41ኤሌባማ መስፍን፥ ኤላ መስፍን፥ ፊኖን መስፍን፥ 42ቄኔዝ መስፍን፥ ቴማን መስፍን፥ ሜብሳር መስፍን፥ 43መግዴኤል መስፍን፥ ኤራም መስፍን፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም መሳፍንት ናቸው። የኤዶማውያንም አባት ይህ ዔሳው ነው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 36: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in