ኦሪት ዘፀአት 40
40
ድንኳኑ ተተክሎ ለአገልግሎት መዋሉ
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 2“በመጀመሪያው ወር በፊተኛው ቀን የምስክሩን ድንኳን ትተክላለህ። 3በእርሱም ውስጥ የምስክሩን ታቦት ታኖራለህ፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ትጋርዳለህ። 4ገበታውንም ታገባለህ፤ በሥርዐቱም ታሰናዳዋለህ፤ መቅረዙንም አግብተህ ቀንዲሎቹን ትለኵሳለህ። 5የወርቁንም ማዕጠንት በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፤ በድንኳኑም ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ትጋርዳለህ። 6ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውንም መሠዊያ በምስክሩ ድንኳን ደጅ ፊት ታኖረዋለህ። 7የመታጠቢያውን ሰንም በምስክሩ ድንኳንና በመሠዊያው መካከል ታኖረዋለህ፤ በውስጡም ውኃ ትጨምርበታለህ። 8በዙሪያውም አደባባዩን ትሠራለህ፤ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ትዘረጋለህ።#ምዕ. 40 ቍ. 7 እና 8 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 9የቅብዐቱንም ዘይት ወስደህ ድንኳኑን፥ በውስጥዋም ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፤ እርስዋንም ዕቃዋንም ሁሉ ትቀድሳለህ፤ ቅድስትም ትሆናለች። 10ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆነውን መሠዊያ፥ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል። 11የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም ቀብተህ ትቀድሳለህ። 12አሮንንና ልጆቹንም ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ። 13ለአሮንም የተቀደሰውን ልብስ ታለብሰዋለህ፤ ትቀባዋለህ፤ ትቀድሰውማለህ፤ ካህንም ይሆነኛል። 14ልጆቹንም ታቀርባቸዋለህ፤ ቀሚሳቸውንም ታለብሳቸዋለህ፤ 15አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ ካህናትም ይሆኑኛል። ይህም ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም የክህነት ቅብዐት ይሆንላቸዋል።” 16ሙሴም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ እንዲሁም አደረገ።
17እንዲህም ሆነ፤ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት በፊተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ድንኳንዋ ተተከለች። 18ሙሴም ድንኳንዋን ተከለ፤ እግሮችዋንም አኖረ፤ ሳንቆችዋንም አቆመ፤ መወርወሪያዎችዋንም አደረገባቸው፤ ምሰሶዎችዋንም አቆመ። 19እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው መጋረጃውን በድንኳኑ ላይ ዘረጋው፤ የድንኳኑንም መደረቢያ በላዩ አደረገበት።
20ሙሴም ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፤ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አደረገ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው። 21ታቦቷንም ወደ ድንኳኑ አገባ፥ የሚሸፍነውንም መጋረጃ አድርጎ የምስክሩን ታቦት ሸፈነ።
22እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ገበታውን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ ከመጋረጃው ውጭ በድንኳኑ በመስዕ በኩል አኖረው፤ 23ኅብስተ ገጹንም በላዩ በእግዚአብሔር ፊት አሰናዳ።
24እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው መቅረዙን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በገበታውም ፊት ለፊት፥ በድንኳኑ በአዜብ በኩል አኖረ፤ 25ቀንዲሎቹንም በእግዚአብሔር ፊት አበራ።
26እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የወርቁን ማዕጠንት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በመጋረጃው ፊት አኖረ። 27የአዘጋጀውንም ዕጣን ዐጠነበት።
28ሙሴም እግዚአብሔር እንደ አዘዘው በድንኳኑ ደጅ ፊት መጋረጃውን ዘረጋ። 29ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያም በምስክሩ ድንኳን ደጅ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በላዩ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን አቀረበ።
30የመታጠቢያውንም ሰን በምስክሩ ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኖረ፤ ለመታጠቢያም ውኃን ጨመረበት። 31በእርሱም ሙሴና አሮን፥ ልጆቹም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ታጠቡ፤ 32እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ወደ ምስክሩ ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠዊያውም በቀረቡ ጊዜ ይታጠቡ ነበር።#ምዕ. 40 ቍ. 28፥ 30፥ 31 እና 32 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
33በድንኳኑና በመሠዊያውም ዙሪያ አደባባዩን ሠራ፤ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ዘረጋ። እንዲሁም ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።
የእግዚአብሔር ክብር ድንኳኑን እንደ ሞላው
(ዘኍ. 9፥15-23)
34ደመናውም የምስክሩን ድንኳን ከደነ፤ ድንኳንዋም የእግዚአብሔርን ክብር ተሞላች። 35ደመናውም በላዩ ስለነበር ድንኳኑም የእግዚአብሔርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም። 36ደመናውም ከድንኳኑ በተነሣ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በየነገዳቸው#ዕብ. “መንገዳቸውን” ይላል። ይጓዙ ነበር። 37ደመናው ካልተነሣ ግን ደመናው እስከሚነሣበት ቀን ድረስ አይጓዙም ነበር። 38ደመና በቀን በድንኳኑ ላይ ነበርና፥ እሳቱም በሚጓዙበት ሁሉ በሌሊት በእስራኤል ሁሉ ፊት በእርስዋ ላይ ነበርና።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 40: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in