YouVersion Logo
Search Icon

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 12

12
በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ላይ የደ​ረሰ ተጨ​ማሪ ስደት
1በዚ​ያም ወራት ሄሮ​ድስ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ሹሞች ያዛ​ቸው፤ መከ​ራም አጸ​ና​ባ​ቸው። 2የዮ​ሐ​ን​ስ​ንም ወን​ድም ያዕ​ቆ​ብን በሰ​ይፍ ገደ​ለው። 3አይ​ሁ​ድ​ንም ደስ እን​ዳ​ላ​ቸው አይቶ ጴጥ​ሮ​ስን ደግሞ ያዘው፤ ያን​ጊ​ዜም የፋ​ሲካ በዓል ነበር። 4#ዘፀ. 12፥1-27። ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር። 5ጴጥ​ሮ​ስ​ንም በወ​ኅኒ ቤት ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ዘወ​ትር ስለ እርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር።
መል​አክ ጴጥ​ሮ​ስን ከወ​ኅኒ ቤት እንደ አወ​ጣው
6ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር። 7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወርዶ በአ​ጠ​ገቡ ቆመ፤ በቤ​ትም ውስጥ ብር​ሃን ሆነ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንም ጎኑን ነክቶ ቀሰ​ቀ​ሰ​ውና፥ “ፈጥ​ነህ ተነሥ” አለው፥ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ቹም ከእ​ጆቹ ወል​ቀው ወደቁ። 8መል​አ​ኩም፥ “ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፥ ጫማ​ህ​ንም ተጫማ” አለው፤ እንደ አዘ​ዘ​ውም አደ​ረገ፤ “ልብ​ስ​ህ​ንም ልበ​ስና ተከ​ተ​ለኝ” አለው። 9ተከ​ት​ሎ​ትም ወጣ፤ ጴጥ​ሮስ ግን ራእይ የሚ​ያይ ይመ​ስ​ለው ነበረ እንጂ በመ​ል​አኩ የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር እው​ነት እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም ነበር። 10መጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንና ሁለ​ተ​ኛ​ውን ዘብ አል​ፈው ወደ ከተማ ወደ​ም​ት​ወ​ስ​ደው ወደ ብረቱ መዝ​ጊያ ደረሱ፤ ያን​ጊ​ዜም መዝ​ጊ​ያው ራሱ ተከ​ፈ​ተ​ላ​ቸው፤ ወጥ​ተ​ውም በአ​ንድ ስላች መን​ገድ ሄዱ፤ መል​አ​ኩም ጴጥ​ሮ​ስን ትቶት ሄደ። 11ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ። 12ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ። 13ጴጥ​ሮ​ስም በሩን አን​ኳኳ፤ ሮዴ የም​ት​ባል ብላ​ቴ​ናም ልት​ከ​ፍ​ት​ለት መጣች። 14የጴ​ጥ​ሮ​ስም ድምፅ መሆ​ኑን ዐውቃ ከደ​ስታ የተ​ነሣ አል​ከ​ፈ​ተ​ች​ለ​ትም፤ ነገር ግን ጴጥ​ሮስ በበር ቆሞ ሳለ ሮጣ ነገ​ረ​ቻ​ቸው። 15እነ​ር​ሱም “አብ​ደ​ሻ​ልን? አንድ ጊዜ ታገሺ”#“አንድ ጊዜ ታገሽ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አሉ​አት፤ እር​ስዋ ግን እርሱ እንደ ሆነ ታረ​ጋ​ግጥ ነበር። እነ​ር​ሱም፥ “ምና​ል​ባት መል​አኩ ይሆ​ናል” አሉ። 16ጴጥ​ሮስ ግን በሩን ማን​ኳ​ኳ​ቱን ቀጠለ፤ ከፍ​ተ​ውም ባዩት ጊዜ ተደ​ነቁ። 17እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
18በነጋ ጊዜም ወታ​ደ​ሮች፥ “ጴጥ​ሮስ ምን ሆነ?” ብለው ታወኩ። 19ሄሮ​ድስ ግን አስ​ፈ​ልጎ ባጣው ጊዜ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን መረ​መረ፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ አዘዘ፤ ከዚ​ህም በኋላ ከይ​ሁዳ ወደ ቂሳ​ርያ ወርዶ በዚያ ተቀ​መጠ።
የሄ​ሮ​ድስ ሞት
20ሄሮ​ድ​ስም በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ሰዎች ተቈ​ጥቶ ነበር፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ወደ እርሱ መጥ​ተው የን​ጉ​ሡን ቢት​ወ​ደድ በላ​ስ​ጦ​ስን እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸው ማለ​ዱት፤ የሀ​ገ​ራ​ቸው ምግብ ከን​ጉሥ ሄር​ድስ ነበ​ርና። 21ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮ​ድስ ልብሰ መን​ግ​ሥ​ቱን ለብሶ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ተገ​ኝቶ ይፈ​ርድ ጀመረ። 22ሕዝ​ቡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው፤ የሰው ቃልም አይ​ደ​ለም” እያሉ ጮኹ። 23ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ። 24የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ አለ፤ በዛም። 25በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in