YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 13

13
በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ የተ​ደ​ረገ ጦር​ነት
1ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ከነ​ገሠ ሁለት ዓመት ሆነው፥#“ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ከነ​ገሠ ሁለት ዓመት ሆነው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 2ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ። 3ዮና​ታ​ንም በኮ​ረ​ብ​ታው የነ​በ​ሩ​ትን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ መታ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ያን ሰሙ፤ ሳኦ​ልም፦ እስ​ራ​ኤል ይስሙ ብሎ በሀ​ገሩ ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ነፋ። 4እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሳኦል የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግ​ሞም እስ​ራ​ኤል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ዘንድ እንደ በረቱ ሰሙ፤ ሕዝ​ቡም ደን​ፍ​ተው ሳኦ​ልን ለመ​ከ​ተል ወደ ጌል​ጌላ ተሰ​በ​ሰቡ።
5ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ። 6የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ወደ እነ​ርሱ መሄድ እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋ​ሻና በግ​ንብ፥ በገ​ደ​ልና በቋ​ጥኝ፥ በጕ​ድ​ጓ​ድም ውስጥ ተሸ​ሸጉ። 7ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግ​ረው ወደ ጋድና ወደ ገለ​ዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌ​ል​ጌላ ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው እር​ሱን መከ​ተ​ልን ትተው ተበ​ተኑ።
ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን እንደ ገሠ​ጸው
8ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ቀጠ​ረው ጊዜ ሰባት ቀን ቈየ፤ ሳሙ​ኤል ግን ወደ ጌል​ጌላ አል​መ​ጣም፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ታ​ተኑ። 9ሳኦ​ልም፥ “የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት አም​ጡ​ልኝ” አለ። የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ። 10የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም እን​ዲ​ባ​ር​ከው ሊገ​ና​ኘው ወጣ። 11ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አለ። ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለ​ይ​ተው እንደ ተበ​ታ​ተኑ፥ አን​ተም በነ​ገ​ር​ኸኝ መሠ​ረት በቀ​ጠ​ሮው ቀን እን​ዳ​ል​መ​ጣህ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ማኪ​ማስ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አየሁ፤ 12ስለ​ዚህ፦ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አሁን ወደ እኔ ወደ ጌል​ጌላ ይወ​ር​ዱ​ብ​ኛል፤ እኔም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት አል​ለ​መ​ን​ሁም አልሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደፍሬ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን አሳ​ረ​ግሁ” አለ። 13ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በድ​ለ​ኻል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛ​ዙን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ት​ህን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ን​ቶ​ልህ ነበር። 14ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ግን መን​ግ​ሥ​ትህ አይ​ጸ​ናም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መር​ጦ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ንጉ​ሥን ያነ​ግ​ሣል” አለው።
15ሳሙ​ኤ​ልም ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሊገ​ናኙ ሄዱ። ከጌ​ል​ጌ​ላም ተነ​ሥ​ተው ወደ ብን​ያም ገባ​ዖን መጡ፤ ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድ​ስት መቶም የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ። 16ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ተቀ​ም​ጠው አለ​ቀሱ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ። 17ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር ማራ​ኪ​ዎች በሦ​ስት ክፍል ሆነው ወጡ፤ አን​ዱም ክፍል በጎ​ፌር#ዕብ. “ዖፍራ” ይላል። መን​ገድ ወደ ሦጋክ ምድር ሄደ። 18ሁለ​ተ​ኛው ክፍል ወደ ቤቶ​ሮን መን​ገድ ዞረ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ክፍል በገ​ባ​ዖን መን​ገድ ባለው ወደ ሴቤ​ሮም ሸለቆ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በዳ​ር​ቻው መን​ገድ ዞረ።
19ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ዕብ​ራ​ው​ያን ሰይ​ፍና ጦር እን​ዳ​ይ​ሠሩ” ብለው ነበ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አል​ተ​ገ​ኘም። 20እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ማረ​ሻ​ው​ንና ማጭ​ዱን፥ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንና መቈ​ፈ​ሪ​ያ​ውን ይስሉ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ርዱ ነበር። 21አዝ​መ​ራ​ውም ለአ​ጨዳ ደርሶ ነበር። ለማ​ረ​ሻ​ውና ለመ​ቈ​ፈ​ሪ​ያው ዋጋው ሦስት ሰቅል ነበር። መጥ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም ለማ​ሳል፥ መው​ጊ​ያ​ው​ንም ለማ​በ​ጀት ዋጋው ተመ​ሳ​ሳይ ነበር። 22ስለ​ዚ​ህም በማ​ኪ​ማስ ጦር​ነት ጊዜ ሰይ​ፍና ጦር ከሳ​ኦ​ልና ከዮ​ና​ታን ጋር በነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ እጅ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ብቻ በሳ​ኦ​ልና በልጁ በዮ​ና​ታን ዘንድ ተገኘ። 23ከዚ​ያም ጥቂ​ቶች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ወደ ማኪ​ማስ መተ​ላ​ለ​ፊያ ወጡ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in