YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 13

13
ስለ ፍቅር
1የሰ​ውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ እን​ደ​ሚ​ጮህ ነሐስ፥ ወይም እን​ደ​ሚ​መታ ከበሮ#ግሪኩ “እን​ደ​ሚ​ን​ሿ​ሿው ጸና​ጽል” ይላል። መሆኔ ነው። 2#ማቴ. 17፥20፤ 21፥21፤ ማር. 11፥23። ትን​ቢት ብና​ገር፥ የተ​ሰ​ው​ረ​ውን ሁሉ፥ ጥበ​ብ​ንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍ​ለስ የሚ​ያ​ደ​ርስ ፍጹም እም​ነ​ትም ቢኖ​ረኝ ፍቅር ከሌ​ለኝ ከንቱ ነኝ። 3ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ለም​ጽ​ዋት ብሰጥ፥ ሥጋ​ዬ​ንም ለእ​ሳት መቃ​ጠል ብሰጥ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም።
4ፍቅር ያስ​ታ​ግ​ሣል፤ ፍቅር ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ናል፤ ፍቅር አያ​ቀ​ና​ናም፤ ፍቅር አያ​ስ​መ​ካም፤ ፍቅር ልቡ​ናን አያ​ስ​ታ​ብ​ይም። 5ብቻ​ዬን ይድ​ላኝ አያ​ሰ​ኝም፤#ግሪኩ “የማ​ይ​ገ​ባ​ውን አያ​ደ​ር​ግም” ይላል። አያ​በ​ሳ​ጭም፤ ክፉ ነገ​ር​ንም አያ​ሳ​ስ​ብም። 6ጽድ​ቅን በመ​ሥ​ራት ደስ ያሰ​ኛል እንጂ፥ ግፍን በመ​ሥ​ራት ደስ አያ​ሰ​ኝም። 7በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።
8ፍቅር ለዘ​ወ​ትር አይ​ጥ​ልም፤ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይሻ​ራ​ልም፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይቀ​ራል፤ የሚ​ራ​ቀ​ቅም ያል​ፋል፤ ይጠ​ፋል።#ምዕ. 13 ከቍ. 4 እስከ 8 ግሪኩ የነ​ገ​ሩን ስም እንደ ሰብ​አዊ በማ​ድ​ረግ “ፍቅር ይታ​ገ​ሣል ... ፍቅር ለዘ​ወ​ትር አይ​ወ​ድ​ቅም ትን​ቢት ቢሆን ግን ይሻ​ራል ልሳ​ኖች ቢሆኑ ይቀ​ራሉ ዕው​ቀ​ትም ቢሆን ይቀ​ራል” ይላል። 9በየ​ገጹ ጥቂት ጥቂት እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ ጥቂት ጥቂት ትን​ቢ​ትም እን​ና​ገ​ራ​ለ​ንና። 10ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ያ ተከ​ፍሎ የነ​በ​ረው ይሻ​ራል። 11እኔ ልጅ በነ​በ​ርሁ ጊዜ እንደ ልጅ እና​ገር ነበር፤ እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እመ​ክር ነበር፤ በአ​ደ​ግሁ ጊዜ ግን የል​ጅ​ነ​ትን ጠባይ ሁሉ ሻርሁ። 12አሁን ግን ታወ​ቀኝ፤ በግ​ል​ጥም ተረ​ዳኝ፤#“ታወ​ቀኝ በግ​ል​ጥም ተረ​ዳኝ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በመ​ስ​ታ​ወ​ትም እን​ደ​ሚ​ያይ ሰው ዛሬ በድ​ን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ እና​ያ​ለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እና​ያ​ለን፤ አሁን በከ​ፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ መጠን ሁሉን አው​ቃ​ለሁ። 13አሁ​ንም እነ​ዚህ ሦስቱ እም​ነት፥ ተስ​ፋና ፍቅር ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤ ከሁሉ ግን ፍቅር ይበ​ል​ጣል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in