YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ዘካርያስ መግቢያ

መግቢያ
የነቢዩ የዘካርያስ መጽሐፍ በሁለት ክፍሎች የተመደበ ነው፤
ከምዕራፍ አንድ እስከ ስምንት የተተነበየው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአምስት መቶ ኻያ እስከ አምስት መቶ ዐሥራ ስምንት ዓመት ባለው ዘመን ውስጥ ነው። መጽሐፉ በተለያዩ ጊዜያት ነቢዩ ዘካርያስ የተናገራቸውን የትንቢት ቃላት የያዘ ክፍል ነው፤ እነዚህም የትንቢት ቃላት በራእይ መልክ የቀረቡ ሲሆን ስለ ኢየሩሳሌም መታደስ፥ ስለ ቤተ መቅደሱ እንደገና መሠራት፥ ስለ እግዚአብሔር ሕዝብ መንጻትና ወደ ፊት ስለሚመጣው የመሢሑ ዘመን የሚናገሩ ናቸው።
2. ከምዕራፍ ዘጠኝ እስከ ዐሥራ አራት ያለው ክፍል ዘግየት ብለው የተነገረውን የትንቢት ቃል የያዘ ነው፤ እነዚህም የትንቢት ቃላት የሚናገሩት ወደ ፊት ስለሚመጣው መሢሕና ስለ መጨረሻው ፍርድ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የመጀመሪያ ራእይ፥ ፈረሶችና ፈረሰኞች (1፥1-17)
ሁለተኛ እና ሦስተኛ ራእይ የእንስሳ ቀንዶች እና መለኪያ ገመድ (2፥1-17)
አራተኛ ራእይ፥ ነቢዩ ዘካርያስ ስለ ሊቀ ካህናቱ ያየው (3፥1-10)
አምስተኛ ራእይ፥ የመቅረዝና የወይራ ዛፎች (4፥1-14)
ስድስተኛ ራእይ፥ በራሪው የመጽሐፍ ጥቅል (5፥1-4)
ሰባተኛ ራእይ፥ በቅርጫት ውስጥ ያለች ሴት (5፥5-11)
ስምንተኛ ራእይ፥ አራት ሠረገሎች (6፥1-8)
ኢያሱን ቀብቶ ለማንገሥ የተሰጠ ትእዛዝ (6፥9-15)
እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነውን ጾም የማይቀበል መሆኑ (7፥1-7)
አለመታዘዝ የስደት ምክንያት መሆኑ (7፥8-14)
እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም የሰጠው ተስፋ (8፥1-23)
እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚያድንና ጠላቶቻቸውን እንደሚቀጣ (9፥1—11፥3)
ሁለቱ የእስራኤል መሪዎች (11፥4-17)
የኢየሩሳሌም ድል አድራጊነት (12፥1-9)
ሕዝቡ በጦር ለተወጋው ማዘኑና ወደ ጌታ መመለሱ (12፥10—13፥9)
የመጨረሻ ጦርነትና የጌታ ድል (14፥1-21)
ምዕራፍ

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in