ትንቢተ ዘካርያስ 4
4
አራተኛ ራእይ፦ መቅረዝና ሁለቱ የወይራ ዛፎች
1ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ መጣና ከእንቅልፌ የምነቃ ያህል ቀሰቀሰኝ። 2#ዘፀ. 25፥31-40፤ 1ነገ. 7፥49፤ ራእ. 11፥4።እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ ይታየኛል፤ የዘይት ማሰሮም በላዩ ላይ ነበረ። በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ። 3በተጨማሪም ሁለት የወይራ ዛፎች፥ አንዱ በማሰሮው በስተ ቀኝ አንዱም በስተ ግራው ነበሩ” አልኩት። 4ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። 5ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውም መልአክ መልሶ፦ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ አላውቅም” አልኩት።
ትንቢት
6 #
ሆሴዕ 1፥7። እርሱም መልሶ፦ “ለዘሩባቤል የተባለው የጌታ ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። 7ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ እርሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል” ብሎ ነገረኝ።
8የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 9የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። 10#ዘካ. 1፥11፤ 6፥7፤ ራእ. 5፥6።የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ።
የዛፎቹና የመቅረዙ ማብራሪያ
“እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።” 11#ኢያ. 3፥11፤ ሚክ. 4፥13፤ ራእ. 11፥4።እኔም መልሼ፦ “በመቅረዙ በስተቀኝና በስተ ግራ ያሉ እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” አልኩት። 12ለሁለተኛ ጊዜም፦ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልኩት። 13እርሱም መልሶ፦ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፦ “ጌታ ሆይ፥ አላውቅም” አልኩት። 14እርሱም፦ “በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ የተቀቡት እነዚህ ናቸው” አለኝ።
Currently Selected:
ትንቢተ ዘካርያስ 4: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in