ወደ ሮሜ ሰዎች 3
3
1እንግዲህ አይሁዳዊው ጥቅሙ ምንድነው? ወይም የመገረዝ ትርፉ ምንድነው? 2በማንኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጣቸው። 3አንዳንዶች ባያምኑስ? የእነሱ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ዋጋ የሌለው ያደርገዋልን? 4#መዝ. 51፥4።በጭራሽ!
“በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤”
ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።#3፥4 የእግዚአብሔር እውነተኛነት ይታይ። 5ነገር ግን ዐመፃችን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያጎላ ከሆነ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በቁጣ ቢቀጣን ትክክል አይደለም ሊባል ነውን? እንደ ሰው እላለሁ። 6በጭራሽ! ያለበለዚያ እግዚአብሔር ዓለምን እንዴት ይፈርዳል? 7ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነተኛነት በእኔ ውሸት ለክብሩ ከሞላ፥ ለምን እኔ እስካሁን እንደ ኃጢአተኛ ይፈረድብኛል? 8“መልካም ነገር እንዲመጣ ለምን ክፉ አናደርግም?” ይላሉ ብለው እንደሚያሙን አይደለም፤ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።
ማንም ጻድቅ የለም
9ስለዚህ ምን ይሁን? እኛ እንበልጣለንን? በጭራሽ! አይሁዳውያንንም ግሪካውያንንም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋል፤ 10#መዝ. 14፥1-3፤ 53፥1-3።እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ
“ጻድቅ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም፤
11የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤
12ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤
በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤
መልካም የሚሠራ አንድም የለም፤ አንድ ስንኳ የለም።”
13 #
መዝ. 5፥9፤ መዝ. 140፥3። “ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም አታለዋል፤”
“የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤”
14 #
መዝ. 10፥7። “አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቷል፤”
15 #
ኢሳ. 59፥7፤8። “እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤
16ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፤
17የሰላምንም መንገድ አያውቁም።”
18 #
መዝ. 36፥1። “በዐይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።”
19ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤ 20#መዝ. 143፥2፤ ገላ. 2፥16።ምክንያቱም በሕግ ሥራ#3፥20 ሕግን ማክበርና መፈጸም ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።
በእምነት በኩል ስለሚገኝ ጽድቅ
21አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤ 22#ገላ. 2፥16።ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ 23ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ 24በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲሁ በጸጋው ይጸድቃሉ። 25እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤ 26ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን እንዲያሳይ ነው።
27ስለዚህ ትምክህት ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ሕግ ነው። 28ሰው ሕግ#3፥28 ሕግ ሲል የኦሪት ሕግ ማለቱ ነው። ከሚያዘው ሥራ ውጭ በእምነት እንደሚጸድቅ እናምናለንና። 29ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን የአሕዛብም አምላክ ነው፤ 30#ዘዳ. 6፥4፤ ገላ. 3፥20።የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አንድ አምላክ አለና። 31ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 3: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in