YouVersion Logo
Search Icon

የዮሐንስ ራእይ 6

6
የሰባቱ ማኅተሞች መፈታት
1በጉም ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ከአራቱም ሕያዋን ፍጡራን አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “ና” ሲል ሰማሁ። 2#ዘካ. 1፥8፤ 6፥3፤6።አየሁም፤ እነሆም ነጭ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድል እየነሣ፥ ድልም ለመንሣት ወጣ።
3ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ “ና” ሲል ሰማሁ። 4#ዘካ. 1፥8፤ 6፥2።ሌላም ደማቅ ቀይ ፈረስ ወጣ፤ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ፥ ሰላምን ከምድር ያስወግድ ዘንድ በእርሱ ላይ ለተቀመጠው ሥልጣን ተሰጠው፤ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።
5 # ዘካ. 6፥2፤6። ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “ና” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ። 6በአራቱም ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንደ ድምፅ ሰማሁ፦ “አንድ እርቦ#6፥6 መስፈርያ። ስንዴ በዲናር#6፥6 የአንድ ቀን ሥራ ደሞዝ። ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንን ግን አትጉዳ” ሲል ሰማሁ።
7አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ “ና” ሲል ሰማሁ። 8#ሕዝ. 14፥21።አየሁም፤ እነሆም የገረጣ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።
9አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክርነት የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። 10በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ። 11ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱም መገደል የሚጠብቃቸውን የሌሎች አገልጋዮች የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪሞላ ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተነገራቸው።
12 # ራእ. 11፥13፤ 16፥18፤ ኢሳ. 13፥10፤ ኢዩ. 2፥10፤31፤ 3፥15፤ ማቴ. 24፥29፤ ማር. 13፥24፤25፤ ሉቃ. 21፥25። ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጉር ጥቁር ሆነች፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነች፤ 13#ኢሳ. 34፥4።በለስም በብርቱ ነፋስ ስትናውጥ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ የሰማይ ከዋክብትም ወደ ምድር ወደቁ፤ 14#ራእ. 16፥20።ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ። 15#ኢሳ. 2፥19፤21።የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም፥ ሀብታሞችም፥ ኃይለኞችም፥ አገልጋዮችም፥ ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሰወሩ፤ 16#ሆሴዕ 10፥8፤ ሉቃ. 23፥30።ተራራዎችንና ዐለቶችንም “በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቁጣ ሰውሩን፤ 17#ኢዩ. 2፥11፤ ሚል. 3፥2።ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ጸንቶ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in