መዝሙረ ዳዊት 76
76
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
2 #
ዕብ. 3፥2። እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥
ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።
3ድንኳኑ በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው።
4 #
መዝ. 46፥10፤ 122፥6-9። በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥
ጋሻን ሰይፍን ሰልፍንም ሰበረ፥
5አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።
6 #
2ነገ. 19፥35፤ ኤር. 51፥39፤ ናሆም 3፥18። ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥
እንቅልፋቸውንም አንቀላፉ፥
የጦር ሰዎች በሙሉ በእጃቸው ምንም ማድረግ አልቻሉም።
7የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ
ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።
8 #
ዘዳ. 7፥21፤ 1ሳሙ. 6፥20፤ ናሆም 1፥6፤ ሚል. 3፥2። አንተ ግን፥ አንተ ግሩም ነህ፥
ቁጣህን ማን ይቃወማል?
9ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፥
ምድር ፈራች ዝምም አለች፥
10የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ
እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።
11የሰውም ቁጣ ሳይቀር ክብርህን ይገልጣል፥
ከዚህ የሚተርፈውንም ትታጠቀዋለህ።
12 #
ዘኍ. 30፥3። ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፥
በዙሪያው ያሉ ሁሉ ለሚያስፈራው እጅ መንሻን ያስገቡ።
13የመኳንንትን ነፍስ ያወጣል፥
በምድርም ነገሥታት ዘንድ ያስፈራል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 76: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in