YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 67

67
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 4፥7፤ 31፥17፤ 44፥4፤ 80፥4፤ ዳን. 9፥17። እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥
ፊቱንም በላያችን ያብራ፥
3 # ኤር. 33፥9። መንገድህንም በምድር፥
በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን እናውቅ ዘንድ።
4አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥
አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።
5 # መዝ. 98፥9። ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥
አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና
አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ።
6አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥
አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።
7 # መዝ. 85፥13፤ ዘሌ. 26፥4፤ ሕዝ. 34፥27፤ ሆሴዕ 2፥23-24። ምድር ፍሬዋን ሰጠች፥
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
8እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in