YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 62

62
1ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር
2 # መዝ. 18፥3፤ 31፥3-4፤ 42፥10፤ 118፥8፤ 146፥3። ነፍሴ በጸጥታ እግዚአብሔርን ትጠብቅ የለምን?
መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
3እርሱ ብቻ ዓለቴና መድኃኒቴም ነው፥
እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ በፍጹም አልታወክም።
4እስከ መቼ በሰው ላይ ትነሣላችሁ?
እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ
እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ።
5 # መዝ. 12፥3፤ 28፥3፤ 55፥22፤ ምሳ. 26፥24-25። ከከፍታ ያናውጡት ዘንድ መከሩ፥
ሐሰትንም ይወድዳሉ፥
በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።
6ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን በጸጥታ ጠብቂ፥
ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
7እርሱ ዓለቴም መድኃኒቴም ነውና፥
እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ አልታወክም።
8 # መዝ. 3፥3፤ ኢሳ. 26፥4፤ 60፥19። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፥
ጠንካራ ዓለቴና መጠለያዬ እግዚአብሔር ነው።
9ሕዝቦች ሆይ፥ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፥
ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥
እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።
10 # መዝ. 39፥6-7፤ 144፥4፤ ኢዮብ 7፥16፤ ጥበ. 2፥5። ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ#62፥10 ቃል በቃል “ትንፋሽ” ማለት ነው ናቸው፥
የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፥
በሚዛንም ይበድላሉ፥
እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።
11 # ኢዮብ 31፥25፤ መክ. 5፥9፤ ኤር. 17፥11፤ ማቴ. 6፥19-21፤ 24። ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥
ቅሚያንም አትተማመኑት፥
ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኩራ።
12 # ኢዮብ 40፥5። እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥
እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፥
ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥
13 # መዝ. 28፥4፤ 31፥24፤ 2ሳሙ. 3፥39፤ ኢዮብ 34፥11፤ ኤር. 17፥10፤ ማቴ. 16፥27፤ ሮሜ 2፥6፤ 2ጢሞ. 4፥14። አቤቱ፥ ቸርነትም ያንተ ነው፥
አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍላለህና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in