YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 6

6
1ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ ስምንተኛ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 38፥2። አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥
በመዓትህም አትገሥጸኝ።
3 # ኤር. 17፥14-15። ዝያለሁና አቤቱ፥ ማረኝ፥
አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
4 # መዝ. 13፥2-3፤ 74፥10፤ 89፥47። ነፍሴም እጅግ ታወከች፥
አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
5አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥
ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
6 # መዝ. 30፥10፤ 88፥11፤ 115፥17፤ ኢሳ. 38፥18። በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥
በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
7በመቃተቴ ደክሜአለሁ፥
ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን በእንባ አጥባለሁ፥
በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
8 # መዝ. 31፥10፤ 38፥11፤ 40፥13። ዓይኔ ከኀዘን ዕንባ የተነሣ ታወከች፥
ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ ደከመች።
9 # መዝ. 119፥115፤ ማቴ. 7፥23፤ ሉቃ. 13፥27። ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥
ጌታ የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
10ጌታ ልመናዬን ሰማኝ፥
ጌታ ጸሎቴን ተቀበለ።
11 # መዝ. 35፥4፤ 26፤ 40፥15፤ 71፥13። ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ እጅግም ይጐስቁሉ፥
ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ በፍጥነትም ይፈሩ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in