YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 58

58
1ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።
2 # መዝ. 82፥2፤ ዘዳ. 16፥19። በእውነት ጽድቅን ትናገራላችሁን፥
ገዢዎች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁን?
3በልባችሁ በምድር ላይ ግፍን ትሠራላችሁና፥
እጆቻችሁም ዐመጽን ይፈጽማሉና።
4ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥
ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።
5 # መዝ. 64፥4፤ 140፥3፤ ሮሜ 3፥13። የእባብ መርዝ ዓይነት መርዝ አላቸው፥
ጆሮውን እንደደፈነ እባብ ናቸው፥
6አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።
7 # መዝ. 3፥7። አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥
የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።
8 # መዝ. 37፥2፤ ጥበ. 16፥29። እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥
ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።#58፥8 አንዳንድ እትሞች “እንደ ሣር ተረግጠው ይጠውልጉ” የሚል ትርጒም ያቀርባሉ
9 # ኢዮብ 3፥16። እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥
ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።
10 # ኢዮብ 21፥18፤ ሆሴዕ 13፥3፤ ናሆም 1፥10። ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።
11 # መዝ. 68፥24፤ ኢሳ. 63፥1-6። ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥
በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል።
12ሰውም፦ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፥
በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in