መዝሙረ ዳዊት 48
48
1በሁለተኛ ሰንበት የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
2 #
መዝ. 96፥4፤ 145፥3። ጌታ ትልቅ ነው፥
በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
3 #
መዝ. 50፥2፤ ሰቆ.ኤ. 2፥15፤ ኢሳ. 14፥13፤ ማቴ. 5፥35። በሰሜን በኩል በመልካም ስፍራ የቆመ
የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፥
እርሷም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነች።
4እግዚአብሔር በአዳራሾችዋ መጠጊያ ሆኖ ይታወቃል።
5እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል።
6እነርሱስ አይተው ተደነቁ፥ ደነገጡ፥ ሸሹም።
7በዚያ እንደ ወላድ ምጥ መንቀጥቀጥ ያዛቸው።
8በኃይለኛ#48፥8 የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ።
9እንደ ሰማን እንዲሁ አየን
በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፥
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።
10አምላክ ሆይ፥ በመቅደስህ ውሰጥ ርኅራኄህን አሰላሰልን።
11 #
ሚል. 1፥11። አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ ምስጋናህም
እንዲሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው፥
ቀኝህ#48፥11 ቀኝ እጅህ ጽድቅን የተሞላች ናት።
12 #
መዝ. 97፥8። አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው፥
የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።
13ጽዮንን ክበቡአት፥
በዙሪያዋም ተመላለሱ፥
ግንቦችዋንም ቁጠሩ፥
14 #
መዝ. 22፥31-32፤ 71፥18። በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥
ቅጥሮችዋን መርምሩ፥
ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።
15ለዓለምና ለዘለዓለም ይህ አምላካችን ነው፥
እርሱም ለዘለዓለም ይመራናል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 48: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in