YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 121

121
1የዕርገት መዝሙር።
# ኤር. 3፥23። ዐይኖቼን ወደ ተራሮቹ አነሣሁ፥
ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
2 # መዝ. 124፥8፤ 146፥6። ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ
ከጌታ ዘንድ ነው።
3 # መዝ. 66፥9፤ 91፥12፤ 1ሳሙ. 2፥9፤ ምሳ. 3፥23። እግርህ እንዲናወጥ አይፈቅድም፥
የሚጠብቅህም አይተኛም።
4እነሆ፥ የእስራኤል ጠባቂ አይተኛም አያንቀላፋምም።
5 # መዝ. 16፥8፤ 73፥23። ጌታ ጠባቂህ ነው፥
ጌታ በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።
6 # ጥበ. 18፥3፤ ኢሳ. 25፥4፤ 49፥10። ፀሐይ በቀን አይመታህም፥ ጨረቃም በሌሊት እንዲሁ።
7 # መዝ. 97፥10። ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥
ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8 # ዘዳ. 28፥6። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
ጌታ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in