YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 118

118
1ሃሌ ሉያ! #መዝ. 100፥5፤ 136፥1።ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥
ፍቅሩም#118፥1 ሰባ ሊቃናት “ምሕረቱ” ይላል። ለዘለዓለም ነውና።
2ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ
የእስራኤል ቤት አሁን ይንገሩ።
3ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ
የአሮን ቤት አሁን ይንገሩ።
4 # መዝ. 115፥9-11። ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ
ጌታን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ።
5በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥
መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።
6 # መዝ. 27፥1፤ ዕብ. 13፥6። ጌታ ከጎኔ ነው፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል?
7ጌታ ሊረዳኝ ከጎኔ ነው፥ እኔም ጠላቶቼን በኩራት አያለሁ።
8 # መዝ. 146፥3። በሰው ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።
9በኃያላን ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።
10አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥
በጌታ ስም አጠፋኋቸው፥
11መክበቡንስ ከበቡኝ፥
በጌታ ስም አጠፋኋቸው።
12 # ዘዳ. 1፥44። ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥
እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፥
በጌታ ስም አጠፋኋቸው።
13 # መዝ. 129፥1-2። ገፈተሩኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፥
ጌታ ግን አገዘኝ።
14 # ዘፀ. 15፥2፤ ኢሳ. 12፥2። ኃይሌም ዝማሬዬም ጌታ ነው፥
እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ።
15የእልልታና የመዳን ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፥
የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ።
16የጌታ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፥
የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ።
17አልሞትም፥ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥
የጌታንም ሥራ እናገራለሁ።
18መገሠጽስ ጌታ ገሠጸኝ፥
ለሞት ግን አልሰጠኝም።
19 # ኢሳ. 26፥2። የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፥
ወደ እነርሱ ገብቼ ጌታን አመሰግናለሁ።
20ይህች የጌታ ደጅ ናት፥
ወደ እርሷ ጻድቃን ይገባሉ።
21ሰምተኸኛልና፥
መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
22 # ማቴ. 21፥42፤ ሉቃ. 20፥17፤ የሐዋ. 4፥11፤ ሮሜ 9፥33። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥
እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፥
23ይህች ከጌታ ዘንድ ሆነች፥
ለዓይናችንም ድንቅ ናት።
24ጌታ የሠራት ቀን ይህች ናት፥
ሐሤትን እናድርግ፥ በእርሷም ደስ ይበለን።
25 # ማቴ. 21፥9፤ ማር. 11፥9፤ ዮሐ. 12፥13። አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፥
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።
26 # ማቴ. 21፥9፤ 23፥39፤ ማር. 11፥9፤ ሉቃ. 13፥35፤ 19፥38፤ ዮሐ. 12፥13። በጌታ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፥
ከጌታ ቤት መረቅናችሁ።
27ጌታ አምላክ ነው፥ ለእኛም አበራልን፥
እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ፥ ቅርንጫፎች ይዘን፥
ለበዓሉ ዑደት እናድርግ#118፥27 ይህ ሐረግ በሌላ መንገድም ይፈታል፦ “የበዓሉን መሥዋዕት በገመድ እሰሩት።”
28አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንሃለሁ።
አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥
ሰምተኸኛልና፥
መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
29ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in