YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 1

1
1 # መዝ. 26፥4-5፤ 40፥5። ብፁዕ ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥
በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥
በፌዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
2 # ኢያ. 1፥8፤ መዝ. 119፤ ሲራ. 39፥1። ነገር ግን በጌታ ሕግ ደስ የሚለው፥
ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ።
3 # መዝ. 52፥10፤ 92፥13-15፤ ኤር. 17፥8። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥
ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥
ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥
የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4 # መዝ. 35፥5፤ 83፥14-16፤ ኢዮብ 21፥18። ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥
ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
5ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥
ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
6 # መዝ. 37፥18። ጌታ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥
የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy