መጽሐፈ ኢያሱ 9
9
በማታለል የገባዖናውያን ራሳቸውን ማዳናቸው
1 #
ኢያ. 3፥10፤ 5፥1፤ ዘፀ. 3፥8፤ 17፤ 23፥23፤ ዘዳ. 1፥7። እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በቈላማውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም፥ ይህን በሰሙ ጊዜ፥ 2ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።
3 #
ኢያ. 6፥21፤ 24። የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ 4እነርሱ ደግሞ ተንኰል አደረጉ፤ ለራሳቸውም ስንቅ ያዙ፥ በአህዮቻቸውም ላይ አሮጌ ዓይበትና ያረጀና የተቀደደ የተጠገነም የወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ። 5ያረጀና የተጠጋገነ ጫማ በእግራቸው አደረጉ አሮጌም ልብስ ለበሱ፤ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ። 6#ዘፀ. 23፥32፤ ዘዳ. 7፥2።ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉ፦ “ከሩቅ አገር መጥተናል፤ እንግዲህ አሁን ከእኛ ጋር የቃል ኪዳን አድርጉ።” 7የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያን እንዲህ አሉአቸው፦ “ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ እንደሆነ እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን?” 8ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ነን።” ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?” 9#ኢያ. 2፥10-11።እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “ከአምላክህ ከጌታ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር ባርያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብጽም ያደረገውን ሁሉ፥ 10#ዘኍ. 21፥25፤33-35፤ ዘዳ. 1፥4።በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። 11ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ እንዲህ አሉን፦ ‘ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥ ልትገናኙአቸውም ሂዱ እንዲህም በሉአቸው፦ “እኛ ባርያዎቻችሁ ነን፤ እንግዲህ አሁን ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ።” ’ 12ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩሱን ለስንቅ ከቤታችን ወሰድነው፤ አሁን ግን እነሆ፥ ደርቆአል፥ ሻግቶአልም፤ 13እነዚህም የወይን ጠጅ አቁማዳዎች አዲስ ሳሉ ሞላንባቸው፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል፤ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።” 14#ዘኍ. 27፥21።የእስራኤልም አለቆች ከስንቃቸው ወሰዱ፥ የጌታንም ምሪት አልጠየቁም። 15#ኢያ. 11፥19፤ 2ሳሙ. 21፥2።ኢያሱም ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲኖሩም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ የማኅበሩም አለቆች ማሉላቸው።
16ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ ጎረቤቶቻቸው እንደ ሆኑ በመካከላቸውም እንደሚኖሩ ሰሙ። 17የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፤ ከተሞቻቸው ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያት-ይዓሪም ነበሩ። 18የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በጌታ ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ። 19አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በእስራኤል አምላክ በጌታ ምለንላቸዋል፤ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም። 20#ኢያ. 22፥20።ስለ ማልንላቸው መሓላ ቁጣ እንዳይወርድብን ይህን እናድርግባቸው፥ በሕይወትም እንዲኖሩ እንተዋቸው።” 21#ዘዳ. 29፥11።አለቆቹም፦ “በሕይወት ይኑሩ” አሉአቸው፤ አለቆቹም እንደ ተናገሩአቸው ለማኅበሩ ሁሉ እንጨት ቆራጮች ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።
22ኢያሱም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ በመካከላችን ስትኖሩ፦ ‘ከእናንተ እጅግ የራቅን ነን’ ብላችሁ ለምን አታለላችሁን? 23እንግዲህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ እናንተም ለአምላኬ ቤት እንጨት ቈራጭ ውኃም ቀጂ ባርያዎች ለዘለዓለም ትሆናላችሁ።” 24#ዘፀ. 23፥27-28፤ ዘዳ. 7፥1-2።መልሰውም ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ በእርሷም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋ ጌታ አምላክህ ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ስለ ፈራን ይህን ነገር አድርገናል። 25እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፤ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን።” 26እንዲሁም አደረገባቸው፥ ከእስራኤልም ልጆች እጅ አዳናቸው፥ አልገደሉአቸውምም። 27በዚያም ቀን ኢያሱ በመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለማኅበሩና ለጌታ መሠዊያ እንጨት ቈራጮች ውኃም ቀጂዎች አደረጋቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 9: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in