ትንቢተ ሆሴዕ 6
6
የንስሐ ጥሪ
1እንዲህም ይላሉ፦ “ኑ፥ ወደ ጌታ እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል። 2ከሁለት ቀን በኋላ ነፍስ ይዘራብናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፥ በፊቱም በሕይወት ያኖረናል። 3እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
የእስራኤልና የይሁዳ አለመጸጸት
4ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ? 5ስለዚህ በነቢያት እጅ ቆረጥኋቸው፥ በአፌም ቃላት ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል። 6#ማቴ. 9፥13፤ 12፥7።ከመሥዋዕት ይልቅ ጽኑ ፍቅርን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወዳለሁና። 7እነርሱ ግን በአዳም ቃል ኪዳንን ተላልፈዋል፤ በዚያም ቦታ እኔን አታለውኛል። 8ገለዓድ በደም የተቀባች የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነች። 9በሰው ላይ እንደሚያደቡ ወንበዴዎች እንዲሁ ካህናት አብረው ተሰበሰቡ፥ ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ ላይ ይገድላሉ፤ በእርግጥም፥ ሴሰኝነትንም ያደርጋሉ። 10በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ዝሙት አለ፥ እስራኤልም ረክሶአል። 11ይሁዳ ሆይ! የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ ለአንተ ደግሞ መከር ተወስኖልሃል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 6: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in