YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ዕብራውያን 3

3
ኢየሱስ ከሙሴ ይበልጣል
1ስለዚህ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ! የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ 2#ዘኍ. 12፥7።ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታመነ እንደሆነ፥ እርሱ ለሾመው የታመነ ነበረ። 3ቤትን የሚሠራው ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው ሁሉ፥ እንዲሁ እርሱ ከሙሴ ይልቅ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተቆጥሮአልና። 4ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው። 5ሙሴም ወደ ፊት መባል ለሚገባው ነገር ለመመስከር፥ እንደ አገልጋይ በመላው በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ ነበር፤ 6ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፥፥ እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ፥ ቤቱ ነን።
የእግዚአብሔር ወገኖች ዕረፍትን ያገኛሉ
7 # መዝ. 94፥7-11። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው፥ ዛሬ ድምፁን ስትሰሙት፥
8በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማመጽ እንደ ሆነው፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። 9አባቶቻችሁ እኔን ፈተኑ፥ ሥራዬን አዩ፥
10ለአርባ ዓመታት፤ ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ “ዘወትር በልባቸው ይስታሉ፤ መንገዴን ግን አላወቁም፤” አልኩ፤
11በቍጣም እንደ ማልሁ፥ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፥”
12ወንድሞች ሆይ! ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ 13ነገር ግን ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ፥ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ፥ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ። 14የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤ 15#መዝ. 94፥7፤8።
“ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” እንደተባለው ነው።
16 # ዘኍ. 14፥1-35። ሰምተው ያመጹት እነማን ነበሩ? በሙሴ ተመርተው ከግብጽ የወጡ ሁሉ አይደሉምን? 17አርባ ዓመትስ የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ፥ ኃጢአትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን? 18ካልታዘዙትም በስተቀር፥ ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ? 19እንግዲህ ባለማመናቸው ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in