ወደ ገላትያ ሰዎች 3
3
እምነት ወይስ የኦሪትን ሕግ መጠበቅ
1እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በዐይኖቻችሁ ላይ ተሥሎ ነበር፤ 2ከእናንተ ይህን ብቻ መማር እፈልጋለሁ፤ መንፈስን የተቀበላችሁት በሕግ ሥራ ነውን? ወይስ በእምነት በመስማት? 3እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን ግን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? 4ይህን ሁሉ መከራ የተቀበላችሁት በከንቱ ነውን? እንደዚያ ከሆነ በእርግጥ ከንቱ ነው። 5እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ድንቅን የሚሠራ፥ በሕግ ሥራ ነውን? ወይስ በእምነት በመስማታችሁ ነው?
6 #
ዘፍ. 15፥6፤ ሮሜ 4፥3። አብርሃም በእግዚአብሔር እንደ አመነና፥ ጽድቅም ሆኖ እንደ ተቆጠረለት፥ 7#ሮሜ 4፥16።እንግዲህ እነዚህ የሚያምኑት፥ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ። 8#ዘፍ. 12፥3።መጽሐፍም፥ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፥ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ፤” ብሎ አስቀድሞ ለአብርሃም ወንጌልን ሰበከለት። 9ስለዚህም የሚያምኑት ከታመነው ከአብርሃም ጋር ተባርከዋል።
10 #
ዘዳ. 27፥26። ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና። 11#ዕን. 2፥4።“ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሏልና፥ ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንደማይጸድቅ ግልጥ ነው። 12#ዘሌ. 18፥5።ሕግ ከእምነት አይደለም፤ ነገር ግን “የሚፈጽማቸው በእነርሱ ይኖራል።” 13#ዘዳ. 21፥23።ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ፥ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል፤ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው፤” ተብሎ ተጽፎአልና 14ይህም የአብርሃም በረከት፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አሕዛብ እንዲደርስና የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል ነው።
የኦሪት ሕግና ተስፋ
15ወንድሞች ሆይ! እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የጸና ኪዳን፥ የሰው ስንኳ ቢሆን፥ ማንም አያፈርሰውም ወይም አይጨምርበትም። 16የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው። 17#ዘፀ. 12፥40።ይህንም እላለሁ፦ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ፥ የተስፋውን ቃል ለማስቀረት፥ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን ሊሽር አይችልም። 18#ሮሜ 4፥14።ውርስ በሕግ ቢሆን ኖሮ፥ በተስፋ ቃል መሆኑ ይቀር ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ለአብርሃም በተስፋ ቃል አማካይነት ሰጠው።
19ታዲያ ሕግ ለምንድን ነው? በተስፋ ቃል የተነገረው ዘር እስኪመጣ ድረስ፥ ስለ መተላለፍ ተጨመረ፤ በመላእክት በኩል መካከለኛ እጅ ታዘዘ። 20መካከለኛው አንድን ወገን ብቻ የሚወክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
ስለ ልጆችና አገልጋዮች
21እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤ 22ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ፥ መጽሐፍ ሁሉን ነገር ከኃጢአት በታች ደምድሞታል።
23እምነት ከመምጣቱ በፊት እምነት እስኪገለጥ ድረስ ተዘግቶብን ከሕግ በታች ሆነን እንጠበቅ ነበር። 24ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ፥ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆነ፤ 25ነገር ግን እምነት ስለ መጣ ከእንግዲህ ወዲህ በሞግዚት ሥር አይደለንም። 26በክርስቶስ ኢየሱስ ባላችሁ እምነት ሁላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ 27ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችሁታል። 28በክርስቶስ ኢየሱስ ሁላችሁም አንድ ናችሁና አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ የለም፥ ባርያ ወይም ነጻ ሰው የለም፥ ወንድ ወይም ሴት የለም። 29#ሮሜ 4፥13።የክርስቶስ ከሆናችሁ ስለዚህ የአብርሃም ዘር ናችሁ፥ በተስፋውም ቃል መሠረት ወራሾች ናችሁ።
Currently Selected:
ወደ ገላትያ ሰዎች 3: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in