YouVersion Logo
Search Icon

2ኛ መጽሐፈ መቃብያን 3

3
የሄልዮድሮስ ታሪክ፥ የሄልዮድሮስ ወደ ኢየሩሳሌም መድረስ
1በዚያን ጊዜ የቅድስት ከተማ ነዋሪዎች በተደላደለ ሰላም ይኖሩ ነበር፤ ሊቀ ካህናትቱ ኦንያ መንፈሳዊና ክፋትን የሚጠላ ስለ ነበር። 2ነገሥታቱም ሳይቀሩ ቅዱሱን ቦታ ያከብሩ ነበር፤ ለቤተ መቅደስም እጅግ ከፍ ያሉ እጅ መንሻዎች ያቀርቡ ነበር። 3እንዲያውም የእስያ ንጉሥ ስለወቀሰው ለመሥዋዕት አገልግሎት የሚያስፈልገውን ከግል ገንዘቡ ወጪ እስከማድረግ ደርሶ ነበር። 4ነገር ግን ከቢልጋ ነገድ የሆነው፥ የቤተ መቅደሱ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው ሰምዖን የተባለ ሰው ስለ ከተማይቱ ሕግ ጉዳይ ከሊቀ ካህናቱ ጋር ሳይስማማ ቀረ። 5ኦንያን ማሸነፍ ስላልቻለ በዚያን ጊዜ የቀለስርያና የፌኒቄስ ሹም ወደነበረው ወደ ተረስያ ልጅ ወደ አጶሎበንዮስ ሄደ፤ 6በኢየሩሳሌም ግምጃ ቤት ውስጥ ተቆጥሮ የማይዘለቅ ሀብት መኖሩንና ይህም ሀብት መኖሩንና ይህም ሀብት ለመሥዋዕቶች ከሚወጣው ገንዘብ ጋር የማይደባለቅ መሆኑን በተጨማሪም ይህን ሀብት ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ማስገባት የሚቻል መሆኑን ነገረው። 7አጶሎንዮስ ለመነጋገር ወደ ንጉሡ በገባ ጊዜ ስለዚህ ሀብት ጉዳይ የተነጋገረውን ገለጸለት፤ ንጉሡ ጠቅላይ አስተዳዳሪውን ሄልዮድሮስን መርጦ ይህንን ሀብት እንዲያመጣ በማዘዝ ላከው። 8ሄልዮድሮስ የቀላሱርያንና የፊኒቴን ከተሞች ለመጐብኘት የሚሄድ አስመስሎ በፍጥነት ሄደ፤ የሄደው ግን የንጉሡን ትዕዛዝ በሥራ ላይ ለማዋል ነበር። 9ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜና በከተማው ውስጥ ሊቀ ካህናቱ የወዳጅነተ አቀባበል ባደረገለት ጊዜ ስለ ሀብቱ ጉዳይ የተነገረውንና እርሱም የመጣበትን ምክንያት ገለጸለት፤ ጉዳዩ እውነት ነው? ሲል ጠየቀው። 10ሊቀ ካህናቱ “ግምጃ ቤት ውስጥ ያለው ገንዘብ ለመበለቶችና ለሙት ልጆች የተቀመጠ ነው” ብሎ መለሰለት፤ 11“እንዲሁም በከፍተኛ ቦታ ላይ ስምዖን እንደ ተናገረው ሳይሆን በጠቅላላው ያለው ገንዘብ አራት መቶ የብር መክሊትና ሁለት መቶ የወርቅ መክሊት ነው። 12በተረፈ ሰዎች በአደራነት በተቀደሰው ቦታ ያስቀመጡትን መንካት በፍጹም የማይቻል ነው፤ ይህም በመላው ዓለም የተከበረው ቤተ መቅደስ እጅግ ታላቅና የማይደፈር በመሆኑ ነው” አለው።
ጭንቀት በኢየሩሳሌም
13ሄልዮድሮስ ግን ከንጉሡ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት እነዚህ ሀብቶች ተወርሰው ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት መግባት አለባቸው ብሎ ቆረጠ። 14በተወሰነው ቀን ሀብቶቹን ለማየትና ለመቁጠር ገባ፤ በዚያን ጊዜ በመላው ከተማ ትልቅ ሁከት ሆነ። 15ካህናት የክህነት ልብሶቻቸውን ለብሰው በመሠዊያው ፊት ተደፍተው በአደራነት ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው እንዳይነካባቸው ጸሎት በማድረግ የአደራ አስቀማጭነትን ሕግ ወዳወጣው አምላክ ልመናቸውን ያቀርቡ ነበር። 16የሊቀ ካህናቱን ፊት የተመለከተ ሁሉ ልቡ በኀዘን ሳይቆስል የቀረ የለም፤ የፊቱ መጐሳቆል የልቡን ኀዘን የሚያመለክት ነበር። 17በመላው ሰውነቱ፥ በእርሱ ላይ የነበረው ፍርሃትና መንቀጥቀጥ ለሚመለከተው ሰው ሁሉ የሰውዬውን የልብ ጭንቀት የሚገልጽ ነበር። 18ይህ የተቃጣው ውርደት ከቅዱስ ቦታ እንዲወገድ በኀብረት ለመጸለይ ሰዎች ተሰብስበው ከየቤታቸው ይወጡ ነበር። 19ሴቶች የተለተለ ልብስ አሸርጠው መንገዶቹን ሞልተው ነበር፤ በቤት የቀሩ ልጃረገዶች፤ አንዳንዶቹ ወደ በሮች፤ አንዳንዶቹ ወደ ግንቦች አጥር እየሮጡ፤ አንዳንዶቹም በየመስኮቱ ብቅ እየሉ 20ሁሉም ወደ ሰማይ እጆቻቸውን ዘርግተው ይጸልዩ ነበር 21የተሰበሰበው ሕዝብ በምድር ላይ ተደፍቶ ሊቀ ካህናቱም በታላቅ ጭንቀት ተይዞ ማየት የሚያሳዝን ነበር። 22ሰዎቹ በአደራነት ያስቀመጡትን ገንዘብ ማንም ሳይነካው ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲጠብቀው ጸሎት በሚደረግበት ጊዜ 23ሄልየድሮስ የታዘዘውን በመፈጸም ላይ ነበር።
የሄልዮድሮስ ቅጣት
24ሄልዮድሮስ ከወታደሮቹ ጋር ሆኖ ግምጃ ቤቱ አጠገብ ነበር። በዚያን ሰዓት የመናፍስትና የኃያላት ሁሉ ጌታ ታየና ሄልዮዶሮስን ለማጀብ ወደዚያ የመጡትና የደፈሩት ሰዎች ሁሉ በአምላክ ኃይል ተመቱ፤ ኃይላቸውና ብርታታቸውም ጠፋ። 25አንድ ፈረስ ታያቸው፤ ፈረሱ በጌጠኛ የፈረስ ዕቃ ተሸልሞ ነበር። በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ሰው እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ፈረሱ በኃይል ወደ ፊት ዘለለና በፊት እግሮቹ ሄልዮድሮስን መታው፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ሰው የወርቅ የጦር መሣሪያ የያዘ ይመስል ነበር። 26በዚያኑ ጊዜ ሁለት ጐልማሶች ለሄልዮድሮስ ታዩት፤ ታላቅ ኃይልና ታላቅ ውበትም ነበራቸው፤ እጅግ ያማረ ልብስም ለብሰው ነበር። በሂልዮድሮስ ግራና ቀኝ ሆነው ያለማቋረጥ ይገርፉት ነበር፤ ግርፋቱን እንደ በረዶ ያወርዱበት ነበር። 27ሄልዮድሮስ ወዲያውኑ በምድር ላይ ወደቀ፤ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማም ለበሰ፤ ሰዎች አንስተው በወሳንሣ ላይ አስቀመጡት፤ 28ተሸክመውም ወሰዱት። ይህ ሰው ከጥቂት ጊዜ በፊት በብዙ ሰዎችና ወታደሮች ታጅቦ ወደ ተባለው ግምጃ ቤት ገብቶ ሰዎች ተሸክመው ወሰዱት። 29ይህ ሰው እንግዲህ በእግዚአብሔር ኃያልነት መናገር ተስኖት፥ ተስፋ ቆርጦ የሚረዳውም አጥቶ ተጋድሞ ነበር። 30አይሁዶች ግን ቅዱስ ቦታውን በተአምር ያከበረውን እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ከጥቂት ጊዜ በፊት በፍርሃትና በችግር ተሞልቶ የነበረው ቤተ መቅደስ ሁሉን የሚል እግዚአብሔር በፍርሃትና በችግር ተሞልቶ የነበረው ቤተ መቅደስ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር በመገለጹ በደስታ ተሞላ። 31ከሂልዮድሮስ ወዳጆች አንዳንዶቹ ወደ ኦንያ ሮጠው ሄዱና ይህን የተጋደመውንና ሊሞት የታቀረበውን ሰው ሁሉን የሚችል አምላክ እንዲያድነው ጸልዩለት ሲሉ ለመኑት። 32ንጉሡ አይሁዳውያን በሂልዮድሮስ ላይ ክፉ መሥዋዕት አቀረረበ። 33ሊቀ ካህናቱ የስርየት መሥዋዕት ሲያቀርቡ ሳለ እነዚያ ጐልማሶች ያንኑ ልብሳቸውን ለብሰው እንደገና ለሂልዮድሮስ ታዩት፤ በአጠገቡ ቆመውም፤ “ሊቀ ካህናቱን ኦንያን በጣም አመስግን፤ ምክንያቱም በእርሱ ምክንያት ነው እግዚአብሔር ሕይወትህን ያዳናት፤ 34በአምላክ የተገረፍህ አንተ ግን ሂድና ታላቁን የአምላክ ኃይል ተናገር” አሉት፤ ይህን ከተናገሩ በኋላ ተሠወሩ። የሄልዮድሮስ መለወጥ 35ሄልዮድሮስ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ካረቀበና ሕይወቱን ላተረፈለት አምላክ ብዙ ስእለት ካደረገ በኋላ ኦንያን በወዳጅነትና በፍቅር ተሰናብቶ ከነሠራዊቱ ወደ ንጉሡ ተመለሰ። 36የታላቁን እግዚአብሔር ሥራና እግዚአብሔርንም በዐይኖቹ ማየቱን በሰዎች ሁሉ ፊት መሰከረ። 37ንጉሡ ሄልዮድሮስን፥ “ወደ ኢየሩሰሌም እንደገና ለመላክ ብቁ የሆነ ማነው” ብሎ ቢጠይቀው እሱም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 38“የአንተ ጠላት የሆነና በመንግሥትህም ላይ የሚዶልት ሰው ካለ እርሱን ላከው፤ በዚያ ቦታ ላይ የአምላክ ኃይል ስላለ የሚላከው ሰው ተገርፎ ይመለስልሃል፤ ያውም ሕይወቱ የተረፈ እንደሆነ ነው። 39ምክንያቱም ይህን ቦታ በሰማይ የሚኖረው አምላክ ይጠብቀዋል፤ ክፉ ለማድረግ አስበው ወደዚያ የሚሄዱትን ሰዎች ይመታቸውና ያጠፋቸዋል።” 40የሄልዮድሮስ ነገርና ግምጃ ቤቱም ምንም አለመነካቱ የተፈጸመው በዚህ ዓይነት ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in