YouVersion Logo
Search Icon

1ኛ የዮሐንስ መልእክት መግቢያ

መግቢያ
የመጀመሪያው የሐዋርያው የዮሐንስ መልእክት ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት። አንደኛ፥ አንባቢዎቹ ከእግዚአብሔርና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት እንዲኖራቸው ለማበረታታት ነው፤ ሁለተኛው ይህንን አንድነት ሊያጠፋ ከሚችል ሐሰተኛ ትምህርት እንዲርቁ ለማስጠንቀቅ ነው። በዚያን ጊዜ የተከሠተው ሐሰተኛ ትምህርት ክፋት የሚመነጨው ከግዙፉ ዓለም ጋር በሚደረገው ግንኙነት ስለሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቶውን ሰው ሊሆን ወይም የሰብአዊነት ባሕርይ ሊኖረው አይችልም የሚል ነበር። እነዚያ መምህራን “መዳን ማለት ለዓለማዊ ኑሮ ከመጨነቅ ነጻ መውጣት ነው” ይሉ ነበር፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ፥ የሥነ ምግባርም ሆነ ለሌላው ሰው ፍቅር ማሳየት ከመዳን ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፥ ይሉ ነበር።
ጸሐፊው ይህን ትምህርት በመቃወም ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ፍጹም አምላክ እንደሆነ ሁሉ፥ ፍጹም ሰውም ነው፤ በኢየሱስ የሚያምኑና እግዚአብሔርን የሚወዱ ሁሉ እርስ በርሳቸውም መዋደድ ይኖርባቸዋል በማለት አስረድቷል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-4)
እግዚአብሔር እንደ ብርሃን (1፥5—3፥10)
እርስ በእርስ ስለ መፋቀር (3፥11—5፥12)
ማጠቃለያ ሐሳብ (5፥13-21)
ምዕራፍ

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in