1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 25
25
የቤተ መቅደሱ መዘምራን
1ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ። 2ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ ነበሩ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ ትእዛዝ በታች ነበሩ። 3ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም ትእዛዝ በታች ነበሩ። 4ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዑዝኤል፥ ሱባኤል፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲ-ዔዘር፥ ዩሽብቃሻ፥ መሎቲ፥ ሆቲር፥ መሐዝዮት ነበሩ፤ 5እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው። 6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም እንዲዘምሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት እንዲያገለግሉ ከአባታቸው ትእዛዝ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ። 7ጌታን ለማወደስ ዜማ የተማሩት ከወንድሞቻቸው ጋር በቊጥር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበሩ። ሁሉም ብልሃተኞች ነበሩ። 8ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ሁሉም በተመሳሳይ መልኩ፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።
9የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 10ሦስተኛው ለዘኩር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 11አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 12አምስተኛው ለነታኒያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 13ስድስተኛው ለቡቅያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 14ሰባተኛው ለይሽርኤል ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 15ስምንተኛው ለየሻያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 16ዘጠኝኛው ለመታንያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለቱ ነበሩ፤ 17አሥረኛው ለሰሜኢ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 19ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሽብያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 21ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 22ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 24ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 25ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 26ዐሥራ ዘጠኝኛው ለመሎቲ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 27ሀያኛው ለኤልያታ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 28ሀያ አንደኛው ለሆቲር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 29ሀያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 30ሀያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ 31ሀያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 25: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in