YouVersion Logo
Search Icon

የዮሐንስ ራእይ መግቢያ

መግቢያ
የዮሐንስ ራእይ የተጻፈው ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታቸው መሆኑን በማመናቸው ምክንያት ስደትና መከራ ይደርስባቸው በነበረ ጊዜ ነው። የጸሐፊው ዋና ትኲረት አንባቢዎቹን ተስፋቸው ሙሉ እንዲሆን ለማበረታታትና በደረሰባቸው ስደትና መከራ ውስጥ በእምነታቸው እንዲጸኑ ለማደፋፈር ነው።
የመጽሐፉ አብዛኛው ክፍል ብዛት ያላቸውና ተከታታይ የሆኑ ራእዮችን የያዘ ነው፤ ራእዮቹም በዚያን ዘመን የነበሩ ምእመናን ሊረዱአቸው የሚችሉ፥ ለሌሎች ግን ምሥጢር ሆነው የሚቈዩ በሥዕላዊ አነጋገር የቀረቡ ናቸው። የመዝሙር አዝማች እንደሚደጋገመው ዐይነት የዚህም መጽሐፍ ርእሶች በተለያዩት ራእዮች አማካይነት በተለያየ መልክ ተደጋግመው ቀርበዋል። ስለ መጽሐፉ አተረጓጐም የተለያየ ሐሳብ ያለ ቢሆንም ዋናው ሐሳብ ግልጥ ነው፤ ይኸውም እግዚአብሔር፥ በጌታ በክርስቶስ በኩል በማያዳግም ሁኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሰይጣንን ጭምር ጠላቶቹን ሁሉ ድል ይነሣል፤ ድሉም በተጠናቀቀ ጊዜ ታማኞች ለሆኑት ወገኖቹ የአዲስ ሰማይንና የአዲስ ምድርን በረከት ያወርሳቸዋል የሚለው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-8
የራእዩ መክፈቻና ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያን የተላከ መልእክት 1፥9—3፥22
መጽሐፉና ሰባቱ ማኅተሞች 4፥1—8፥1
ሰባቱ መለከቶች 8፥2—11፥19
ዘንዶውና ሁለቱ እንስሶች 12፥1—13፥18
የተለያዩ ራእዮች 14፥1—15፥8
ሰባቱ የእግዚአብሔር ቊጣ ጽዋዎች 16፥1-21
የባቢሎን ጥፋት፥ የአውሬው፥ የሐሰተኛው ነቢይና የዲያብሎስ መሸነፍ 17፥1—20፥10
የመጨረሻው ፍርድ 20፥11-15
አዲስ ሰማይ፥ አዲሲቱ ምድር፥ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም 21፥1—22፥5
ማጠቃለያ 22፥6-21

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in