YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 26

26
(የዳዊት መዝሙር)
የደግ ሰው ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ!
በቅንነትና ባለማወላወል በአንተ ተማምኜ ስለ ኖርኩ ፍረድልኝ።
2እግዚአብሔር ሆይ! ፈትነኝ፤
ምኞቴንና ሐሳቤንም መርምር።
3የማያቋርጠው ፍቅርህ በዐይኖቼ ፊት ነው፤
ዘወትር የሚመራኝም የአንተ ታማኝነት ነው።
4ከአታላዮች ጋር አልወዳጅም፤
ከግብዞችም ጋር አልተባበርም፤
5የክፉ አድራጊዎችን ጉባኤ እጠላለሁ፤
ከክፉዎችም ጋር መቀመጥ አልፈቅድም።
6እግዚአብሔር ሆይ!
ንጹሕነቴን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤
መሠዊያህንም በመዞር አንተን አመልካለሁ።
7የምስጋና መዝሙር እየዘመርኩ፥
የአንተን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ እናገራለሁ።
8እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ የምትኖርበትን ቤትና
ክብርህ የሚገኝበትን ስፍራ እወዳለሁ።
9ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤
ሕይወቴንም አታጥፋ።
10እነርሱም ጣቶቻቸው ክፉ ሥራን ለመሥራት የነቁ፥
ቀኝ እጆቻቸውም በጉቦ የተሞሉ ናቸው።
11እኔ በበኩሌ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤
ምሕረትን አድርግልኝ፤ አድነኝም!
12እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤
እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ መዝሙር 26