መጽሐፈ መዝሙር 15
15
እግዚአብሔር ከሰዎች የሚፈልገው ነገር
1እግዚአብሔር ሆይ!
ወደ መኖሪያህ መግባት የሚችል ማን ነው?
በተቀደሰችው ተራራህስ ላይ
ሊኖር የሚችል ማን ነው?
2እርሱ ነቀፋ የሌለበት ሕይወትን የሚኖርና
ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ፥
ከልቡም እውነትን የሚናገር፥
3ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥
በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥
በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥
4ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥
ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥
ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥
5ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥
ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥
እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም።
በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 15: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997