መጽሐፈ መዝሙር 130
130
የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! ከጥልቅ ሐዘን የተነሣ
ወደ አንተ እጮኻለሁ።
2እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ!
ምሕረትህን ፈልጌ ስጮኽም አድምጠኝ!
3ኃጢአታችንን ብትከታተል
ማን ከፍርድ ሊያመልጥ ይችላል?
4ነገር ግን አንተን እንድናከብርህ
ኃጢአታችንን ይቅር ትልልናለህ።
5እግዚአብሔርን በናፍቆት እጠባበቃለሁ፤
በቃሉም እታመናለሁ።
6ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይልቅ
እኔ እግዚአብሔርን በናፍቆት እጠባበቃለሁ።
7እስራኤል ሆይ! ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነና
ሰዎችንም የማዳን ኀይል ያለው ስለ ሆነ
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
8እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን
ከኃጢአታቸው ሁሉ ያድናቸዋል። #ማቴ. 1፥21፤ ቲቶ 2፥14።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 130: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997