መጽሐፈ መዝሙር 125
125
የእግዚአብሔር ወገኖች ዋስትና
1በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሰዎች
ከቶ እንደማይነቃነቅና እንደማይናወጥ
እንደ ጽዮን ተራራ የጸኑ ናቸው።
2ተራራዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ
እንዲሁም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።
3ክፉዎች በጻድቃን ምድር ላይ
የሚዳኙት ለብዙ ጊዜ አይደለም፤
አለበለዚያ ጻድቃንም ክፉ ማድረግን ይጀምራሉ።
4እግዚአብሔር ሆይ!
ትእዛዞችህን ለሚፈጽሙ ደጋግ ሰዎች ቸርነት አድርግላቸው።
5ነገር ግን ክፉ አድራጊዎችን በምትቀጣበት ጊዜ
የአንተን መንገድ የተዉትን
ከሐዲዎችንም አብረህ ቅጣቸው።
ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 125: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997