መጽሐፈ መዝሙር 110
110
እግዚአብሔር የመረጠው ንጉሥ
1እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ)
“ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ
በቀኜ ተቀመጥ” አለው። #ማቴ. 22፥44፤ ማር. 12፥36፤ ሉቃ. 20፥42-43፤ ሐ.ሥ. 2፥34-35፤ 1ቆሮ. 15፥25፤ ኤፌ. 1፥20-22፤ ቆላ. 3፥1፤ ዕብ. 1፥13፤ 8፥1፤ 10፥12-13።
2እግዚአብሔር ኀያል ገዢነትህን ከጽዮን አንሥቶ ያሰፋዋል፤
እንዲህም ይልሃል፦
“በጠላቶችህ ላይ ንገሥ።”
3መግዛት በምትጀምርበት ቀን ሕዝብህ ይገዙልሃል፤
የተቀደሰውን መጐናጸፊያ ደርበህ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት
እንደ ጠል ወለድኩህ።
4እግዚአብሔር “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም
ካህን ትሆናለህ” ብሎ ማለ፤
መሐላውም የማይሻር ነው። #ዕብ. 5፥6፤ 6፥20፤ 7፥17፤21።
5እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፤
በሚቈጣበት ጊዜ ነገሥታትን
ድል ነሥቶ ይሰባብራቸዋል።
6በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤
የጦር ሜዳዎችንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፤
በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ይደመስሳል።
7ንጉሡ ከመንገድ ዳር ካለው ምንጭ ከጠጣ በኋላ፥
ኀይሉን በማደስ በድል አድራጊነት ጸንቶ ይቆማል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 110: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997