ትንቢተ ኢሳይያስ 4
4
1በዚያን ጊዜ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው “በምግብም ሆነ በልብስ ራሳችንን ችለን እንተዳደራለን፤ ‘ባል የላቸውም’ ተብለን ከመሰደብ እንድንድን የአንተ ሚስቶች ተብለን እንድንጠራ ብቻ ፍቀድልን” ብለው ይለምኑታል።
የኢየሩሳሌም እንደገና መታደስ
2በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል። 3በኢየሩሳሌም የተረፉትና በኢየሩሳሌምም እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። 4የኢየሩሳሌምን ርኲሰት ያጠራል፤ በፍርዱና በመንፈሱ ኀይል ደም አፍሳሽነትን ከመኻልዋ ያስወግዳል። 5ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መላውን ከተማና በእዚያም በሚሰበሰቡበት ሁሉ ላይ በቀን ጥቅጥቅ ያለ ደመናን፥ በየሌሊቱም በሚንበለበለው የእሳት ብርሃን ይልካል። የእግዚአብሔርም ክብር ከተማይቱን እንደ ትልቅ ድንኳን ሸፍኖ ይጠብቃታል። #ዘፀ. 13፥21፤ 24፥16። 6የእርሱ ክብር ከተማይቱን ከቀኑ የፀሐይ ቃጠሎ ይጋርዳታል፤ ከዝናብና ከዐውሎ ነፋስ መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናታል።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 4: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997