2 ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት የተነሣው ጥያቄ ሁከት እየፈጠረ በመሄዱ በተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ችግር ተባባሰ፤ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች የጻፈው ሁለተኛው መልእክት “የጌታ መምጫ ቀን ደርሶአል” በሚለው እምነት ላይ ያተኰረ ነበር፤ ጳውሎስም ከክርስቶስ መምጣት በፊት “የዐመፅ ሰው” በተባለው በክርስቶስ ተቃዋሚ መሪነት በዓለም ላይ ክፋትና ዐመፅ እየበዛ ይሄዳል በማለት የእነርሱን እምነት ለማረም ይሞክራል።
ሐዋርያው አንባቢዎቹ መከራና ሥቃይ ቢበዛባቸው እንኳ በእምነታቸው እንዲጸኑ እርሱና ሌሎች የሥራ ተባባሪዎች እንደሚያደርጉት ለኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ለማግኘት ተግተው እንዲሠሩ እንዲሁም መልካም ሥራን ከማድረግ እንዳይቈጠቡ አጥብቆ ይመክራቸዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-2
ምስጋናና ዐደራ 1፥3-12
ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት የተሰጠ ትምህርት 2፥1-17
ስለ ክርስቲያናዊ አኗኗር ምክር 3፥1-15
ማጠቃለያ 3፥16-18
Currently Selected:
2 ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997