ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6
6
የቃል ኪዳኑ ታቦት ከአቢናዳብ ቤት ወደ ኢየሩሳሌም መወሰዱ
(1ዜ.መ. 13፥1-14፤ 15፥25—16፥6፤43)
1ዳዊት እንደገና ከመላው እስራኤል የተመረጡ በድምሩ ሠላሳ ሺህ የሚሆኑ ምርጥ ወታደሮች በአንድነት አሰባሰበ፤ 2ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ። #ዘፀ. 25፥22። 3እነርሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት በኮረብታ ላይ ከሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ አኖሩት፤ ዑዛና አሕዮ ተብለው የሚጠሩት የአቢናዳብ ልጆች ሠረገላውን እየመሩ በሚጓዙበት ጊዜ፥ #1ሳሙ. 7፥1-2። 4አሕዮ ከታቦቱ ፊት ቀድሞ ይሄድ ነበር። 5ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።
6ናኮን ተብሎ ወደሚጠራውም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚስቡት በሬዎች ስለ ነቀነቁት ዑዛ እጁን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት እንዳይወድቅ ደገፈ፤ 7እግዚአብሔር አምላክም ወዲያውኑ ተቈጥቶ ስለ ድፍረቱ ዑዛን ገደለው፤ ስለዚህም ዑዛ በዚያው በቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ ሞተ፤ 8ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የዚያ ስፍራ ስም “ፌሬጽዑዛ” እየተባለ ሲጠራ ይኖራል፤ እግዚአብሔር በቊጣ ተነሣሥቶ ዑዛን በመግደሉ ዳዊት እጅግ ተበሳጨ። #6፥8 ፌሬድ ዑዛ፦ በዕብራይስጥ የዑዛ ስብራት ማለት ነው።
9ከዚያም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ “እንዲህ ከሆነማ የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዴት ልወስደው እችላለሁ?” አለ። 10ስለዚህም ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ላለመውሰድ ወሰነ፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ ከመንገድ መልሶ የጋት ከተማ ነዋሪ ወደ ሆነው ዖቤድኤዶም ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ቤት አስገባው፤ 11እዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ዖቤድኤዶምንና ቤተሰቡን ባረከ። #1ዜ.መ. 26፥4-5።
12በቃል ኪዳኑ ታቦት ምክንያት እግዚአብሔር የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና ያለውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የባረከለት መሆኑን ንጉሥ ዳዊት ሰማ፤ ስለዚህም የቃል ኪዳኑን ታቦት በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ሊወስደው በማሰብ ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዶ አወጣው። 13የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። 14ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ በወገቡ ዙሪያ ታጥቆ እግዚአብሔርን በማክበር በሙሉ ኀይሉ ያሸበሽብ ነበር፤ 15በዚህም ዐይነት ዳዊትና መላው እስራኤል በደስታ እልል እያሉና የእምቢልታ ድምፅ እያሰሙ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ይዘው ሄዱ።
16ታቦቱን ይዘው ወደ ከተማ በሚገቡበት ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት እየዘለለ ሲያሸበሽብ አይታም በልብዋ ናቀችው፤ 17ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ። 18መሥዋዕት ማቅረቡንም በፈጸመ ጊዜ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም ሕዝቡን መረቀ፤ 19ለሁሉም ምግብ አደላቸው፤ በእስራኤል ለሚገኘው ለእያንዳንዱ ወንድና ሴት አንዳንድ ኅብስት፥ አንዳንድ ቊራጭ የተጠበሰ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ ሰጠ፤ ከዚያም በኋላ ሁሉም ወደየቤታቸው ሄዱ።
20ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው። #1ዜ.መ. 16፥43።
21ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “እኔ ያሸበሸብኩት የሕዝቡ የእስራኤል መሪ ያደርገኝ ዘንድ በአባትሽና በቤተሰቡ ፈንታ ለመረጠኝ እግዚአብሔር ክብር ነው፤ አሁንም ቢሆን እርሱን ለማክበር ከመጨፈር አልገታም፤ 22ከዚህም የባሰ ራሴን አዋርዳለሁ፤ ለአንቺ እንደሚመስልሽ በዐይንሽ ፊት የተናቅሁ ብሆንም በእነርሱ ፊት ራስህን አዋረድክ ብለሽ በተናገርሽባቸው ልጃገረዶች ዘንድ እጅግ የተከበርኩ እሆናለሁ!”
23ከዚህም የተነሣ የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም።
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997