ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል። ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ እሺ አትበላቸው፤ “ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤ እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው እንዳሉ እንዋጣቸው፤ ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በየዐይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤ ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣ ልጄ ሆይ፤ አብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤ እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤ ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው። ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣ ምንኛ ከንቱ ነው! እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤ የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው። ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው።
Share
Read ምሳሌ 1
Save verses, read offline, watch teaching clips, and more!
YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy
Home
Bible
Plans
Videos