YouVersion Logo
Search Icon

1 ዜና መዋዕል 16:7-36

1 ዜና መዋዕል 16:7-36 NASV

በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤ ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ። ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤ ዘወትር ፊቱን ፈልጉ። ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤ እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣ እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች። እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤ ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል። ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይስሐቅ የማለውን መሐላ። ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤ እንዲህ ሲል፣ “የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣ የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ።” ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣ በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣ ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ። ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤ እንዲህ ሲል፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤ በነቢያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።” ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ። ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ምስጋናውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው። የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ ብርታትና ደስታም በማደሪያው ስፍራ። የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ክብርና ኀይልን ለእግዚአብሔር አምጡ። ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤ በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ስገዱ። ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም። ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድር ሐሤት ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ። ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናወጥ፤ ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ። ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምድረ በዳ ላይ ሊፈርድ ይመጣልና። ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። “አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ ታደገን፤ ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣ በምስጋናህም እንድንከብር ሰብስበን፤ ከአሕዛብም መካከል ታደገን” ብላችሁ ጩኹ። ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤ እግዚአብሔር ይመስገን” አሉ።

Video for 1 ዜና መዋዕል 16:7-36