1
ኦሪት ዘጸአት 9:16
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ነገር ግን ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ።
Compare
Explore ኦሪት ዘጸአት 9:16
2
ኦሪት ዘጸአት 9:1
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገብተህ ንገረው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
Explore ኦሪት ዘጸአት 9:1
3
ኦሪት ዘጸአት 9:15
አሁን እጄን ዘርግቼ አንተን ሕዝብህንም በቸነፈር በመታሁህ ነበር፤ አንተም ከምድር በጠፋህ ነበር፤
Explore ኦሪት ዘጸአት 9:15
4
ኦሪት ዘጸአት 9:3-4
እነሆ የእግዚአብሔር እጅ በሜዳ ውስጥ ባሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶችም በአህዮችም፥ በግመሎችም፥ በበሬዎችም፥ በበጎችም ላይ ትሆናለች፤ ብርቱ ቸነፈርም ይወርዳል። እግዚአብሔርም በእስራኤልና በግብፅ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንዳች አይጠፋም።’”
Explore ኦሪት ዘጸአት 9:3-4
5
ኦሪት ዘጸአት 9:18-19
እነሆ ነገ በዚህ ጊዜ፥ ከተመሰረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግብፅ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ታላቅ በረዶ አዘንብብሃለሁ። በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንሰሳ ሁሉ በረዶ ወርዶበት ይሞታልና አሁን እንግዲህ ላክ፤ ከብቶችህንም በሜዳም ያለህን ሁሉ አስቸኵል።’”
Explore ኦሪት ዘጸአት 9:18-19
6
ኦሪት ዘጸአት 9:9-10
እርሱም በግብፅ አገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፥ በግብፅም አገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቁስል ይሆናል አላቸው፤” ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ።
Explore ኦሪት ዘጸአት 9:9-10
Home
Bible
Plans
Videos