1
ኦሪት ዘዳግም 28:1
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
Compare
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:1
2
ኦሪት ዘዳግም 28:2
የአምላክህንም የእግዚአብሔር ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል፤ ያገኙህማል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:2
3
ኦሪት ዘዳግም 28:13-14
ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:13-14
4
ኦሪት ዘዳግም 28:12
እግዚአብሔርም ለምድርህ በወራቱ ዝናብ ይሰጥ ዘንድ፥ የእጅህንም ሥራ ሁሉ ይባርክ ዘንድ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል፤ ለብዙ አሕዛብም ታበድራለህ፥ አንተ ግን ከማንም አትበደርም።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:12
5
ኦሪት ዘዳግም 28:7
እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:7
6
ኦሪት ዘዳግም 28:8
እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጎተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:8
7
ኦሪት ዘዳግም 28:6
አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:6
8
ኦሪት ዘዳግም 28:3
አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:3
9
ኦሪት ዘዳግም 28:4
የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም ርቢ፥ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:4
10
ኦሪት ዘዳግም 28:9
የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትጠብቅ፥ በመንገዱም ብትሄድ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለልህ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:9
11
ኦሪት ዘዳግም 28:5
እንቅብህና ቡሃቃህ ቡሩክ ይሆናል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:5
12
ኦሪት ዘዳግም 28:11
እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ እግዚአብሔር በጎነቱን በላይህ ያበዛል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:11
13
ኦሪት ዘዳግም 28:10
የምድር አሕዛብም ሁሉ የእግዚአብሔር ስም በአንተ ላይ እንደ ተጠራ አይተው ይፈሩሃል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:10
14
15
ኦሪት ዘዳግም 28:15
ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 28:15
Home
Bible
Plans
Videos