1
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:37
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አቤቱ፥ አንተ አምላክ እንደ ሆንህ፥ ልባቸውንም ደግሞ እንደ መለስህ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፤ አቤቱ፥ ስማኝ፤” አለ።
Compare
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:37
2
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:36
የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ነቢዩ ኤልያስ ቀርቦ “አቤቱ፥ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ! አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ፥ ይህንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጥ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:36
3
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:21
ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በኣል ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:21
4
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:38
የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕቱንም፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ አፈሩንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውሃ ላሰች።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:38
5
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:39
ሕዝቡም ሁሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግምባራቸው ተደፍተው “እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው! እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው!” አሉ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:39
6
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:44
በሰባተኛውም ጊዜ “እነሆ፥ የሰው እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባሕር ወጣች፤” አለ። እርሱም “ወጥተህ አክዓብን ‘ዝናብ እንዳይከለክልህ ሠረገላን ጭነህ ውረድ፤’ በለው፤” አለ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:44
7
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:46
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም አሸንፍጦ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:46
8
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:41
ኤልያስም አክዓብን “የዝናቡ ውሽንፍር እጅግ ነውና ተነሥተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም፤” አለው።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:41
9
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:43
ብላቴናውንም “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት፤” አለው። ወጥቶም ተመልክቶም፥ “ምንም የለም፤” አለ። እርሱም “ሰባት ጊዜ ተመላለስ፤” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:43
10
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:30
ኤልያስም ሕዝቡን ሁሉ “ወደ እኔ ቅረቡ፤” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ። ፈርሶ የነበረውንም የእግዚአብሔርን መሠዊያ አበጀ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:30
11
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:24
እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ “ይህ ነገር መልካም ነው፤” ብለው መለሱ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:24
12
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:31
ኤልያስም “ስምህ እስራኤል ይሆናል፤” የሚል የእግዚአብሔር ቃል እንደ ደረሰለት እንደ ያዕቆብ ልጆች ነገድ ቁጥር ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ወሰደ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:31
13
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:27
በቀትርም ጊዜ ኤልያስ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት አሳብ ይዞታል፤ ወይም ፈቀቅ ብሎአል፤ ወይም ወደ መንገድ ሄዶአል፤ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል፤” እያለ አላገጠባቸው።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:27
14
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:32
ከድንጋዮችም ለእግዚአብሔር ስም መሠዊያ ሠራ፤ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት መስፈሪያ እህል የሚይዝ ጕድጓድ ቆፈረ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:32
Home
Bible
Plans
Videos