1
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን ለይቶ እንደ አስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ።
Compare
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:10
በልቡ የሚያምን ይጸድቃልና፤ በአፉም የሚመሰክር ይድናልና።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:10
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:17
ማመን ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:17
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:11-13
መጽሐፍ፥ “የሚያምንበት ሁሉ አያፍርም” ብሎአል። አይሁዳዊንና አረማዊን አልለየም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ እግዚአብሔር ባለጸጋ ስለሆነ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና። “የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:11-13
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:15
“መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው?” ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ?
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:15
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:14
ነገር ግን ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:14
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 10:4
የኦሪት ጽድቅ ፍጻሜስ ለሚያምኑበት ሁሉ በክርስቶስ ማመን ነው።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 10:4
Home
Bible
Plans
Videos