1
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:7
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መልካሙን ውጊያ ተዋግቻለሁ፤ የሩጫውን ውድድር ጨርሼአለሁ፤ እምነትን ጠብቄአለሁ፤
Compare
Explore 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:7
2
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:2
ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ተግተህ ሥራ፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።
Explore 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:2
3
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:3-4
ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና። ከቶም እውነትን ከመስማት ጆሮዎቻቸውን ይመልሳሉ፤ መንገድንም ስተው ወደ ተረት ፈቀቅ ይላሉ።
Explore 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:3-4
4
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:5
አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን በትዕግስት ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህን ሙሉ ለሙሉ ፈጽም።
Explore 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:5
5
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:8
ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።
Explore 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:8
Home
Bible
Plans
Videos