1
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:8
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
Compare
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:8
2
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:10
የእግዚአብሔርን ልዩ ልዩ ጸጋ መልካም መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:10
3
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:11
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:11
4
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:16
ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት ግን ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:16
5
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:7
የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል፤ እንግዲህ መጸለይ እንድትችሉ የረጋ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በመጠንም ኑሩ።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:7
6
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:12-13
ወዳጆች ሆይ! እንደ እሳት በሚፈትን መከራ ውስጥ ስትገኙ ያልተለመደ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ አድርጋችሁ አትደነቁ። ይልቅስ የእርሱ ክብር በሚገለጥበት ጊዜ ደግሞ ደስ ብሎአችሁ ኀሤት እንድታደርጉ የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በሆናችሁበት መጠን ደስ ይበላችሁ።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:12-13
7
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:9
ያለ ማጉረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነትን ተቀባበሉ።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:9
8
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:19
ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:19
9
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:1-2
እንግዲህ ክርስቶስ በሥጋ ስለ እኛ መከራን በመቀበሉ፥ እናንተም በዚህ ሐሳብ ራሳችሁን አስታጥቁ፤ ምክንያቱም በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል። ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት አትኑሩ።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:1-2
10
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:14
ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ፥ የእግዚአብሔር የክብሩም መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።
Explore 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:14
Home
Bible
Plans
Videos